Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 7, 2015

የወያኔ መንግስት በአለም አቀፍ ዙሪያ የሚገኙ የራሱ ደጋፊ ዲያስፖራዎችን ሰበሰበ








ዜና ዲያስፖራ ከወደ አዲስ አበባ
በቅርቡ ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ መንግስት በአለም አቀፍ ዙሪያ የሚገኙ ዲያስፖራዎችን በተለይም በሰዉ ሐገር ለፍተዉ ነዋየ ሐብት ያካበቱ የራሱ ደጋፊዎችን ወደ ሐገር ቤ/ት በመጥራት የዲያስፖራ እለት በሚል ብሂል ለ 5 ቀናት አክብሯል። እነዚሁ የወያኔ ጀሌዎች ወይም ዲያስፖራ ተብዬዎች ለያንዳዳቸዉ ካሉበት ሐገር ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የደርሶ መልስ ቲኬታቸዉን ግማሽ ክፍያ የቻለዉ ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ በተደራቢነት ለያንዳዳቸዉ እንደየ ፖለቲካ ጥቅም እሴታቸዉ የመሬትና የተለያዩ ትሩፋቶችን አበርክቷል። ወያኔ በዉችዉ አለም የሚደርስበትን ወይም እየደረሰበት ያለዉን ተቃዉሞ ለመቀልበስ ያስችለኛል በሚል መልኩ የሐገርና የህዝብን ሐብት ያለአግባብ ለደጋፊዎቹ ዲያስፖራ እየቸረዉ ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለይ በዚህ በ2015 ይህንን ለዲያስፖራዎች የቀረበዉን ስጦታ ለመቀበል ወደ ሐገር ቤ/ት ከተጓዙት ግለሰቦች አብዛኛዎቹ ወደመጣንበት ስንመለስ የሚደርስብንን ቻና መሸከም ስለሚከብደን ፎቶዋችንና ቪዲዮዋችን እንዳይለቀቅ የሚል ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን የወያኔዉ ሚኒስቴር የሆነዉ ” ደዋነዉ ከዲር ” የሚባል ባለስልጣን እነማን ናቸዉ የሚያስቸግራችሁ በያሉበት ሐገር ስም ዝርዝራቸዉን ስጡን? የሚል ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ” ዶ/ር አለባቸዉ በየነ ” የተባለ ግለሰብ ይህን ጉዳይ በተመለከተ በጥብቅ እየሰራን ነዉ በማለት ዲያስፖራዎቹን በተናጥል አነጋግሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ በተለይም ወደ አፍሪካ ሐገር የሚኖሩ የወያኔ ደጋፊ ዲያስፖራዎች ወደ መጡበት እንዳይመለሱ የሚያዝ ድንገተኛና አስደጋጭ ትእዛዝ የደረሳቸዉ ሲሆን ይህዉም ለደህንነታችሁ ነዉ ተብለዋል።
የወገኖቻችንን ብሎም የሐገራችንን ሐብትና ንብረት የሚመዘብሩና የመዘበሩ ሁሉ ለፍርድ የሚቀርቡበት እለት እሩቅ አይደለም
።።።።።።።።ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ።።።።።።።።።።፡
ጉድሽ ወያኔ

No comments:

Post a Comment

wanted officials