Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, August 18, 2015

የደቡብ ሱዳን ኢንፎርሜሽን ሚኒስር ስዩም መስፍንን ከሰሱ፡፡

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የኢጋድ ዋነኛ አደራዳሪ የሆኑትን ኢትዮጵያዊውን አምባሳደር ስዩም መስፍንን ከሰሱ፡፡ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ማይክል ማኩኢ በአምባሳደር ስዩም መስፍን ላይ ጠንከር ያለ ወቀሳ ከመሰንዘር በተጨማሪም የኢጋድን የድርድር አካሄድ ወቅሰዋል፡፡
ከስምምነት ላይ የግዴታ መድረስ አለባችሁ ሲል ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሀይላት ላይ ያስቀመጠውን ማሳሰቢያ የድርድር አካሄድ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ ኢጋድም ሆነ አምባሳደር ስዩም መስፍን ‘መመሪያ ሰጪ ሳይሆኑ አሸማጋዮች ናቸው፤ በማሸማገል ሂደት ውስጥ ደግሞ እንዲህ ያለው አካሄድ ተቀባይነት የለውም’ ሲሉ ነው ተቃውሞአቸውን ያሰሙት፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials