Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 19, 2017

ዛምቢያ 147 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው መለሰች


 ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ወደ ዛንቢያ ገብተዋል ያላቸውን በእስር ላይ የነበሩ 147 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የአገሪቱ የስደተኞች ባለስልጣን መስሪያ ቤት አስታውቋል። ስደተኞቹ እ.ኤ.አ. 2016 ጀምሮ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ ተይዘው በተለያዩ የዛንቢያ እስር ቤቶች ውስጥ በግዞት አሳልፈዋል።
ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ባለፈው ወር የእስራት ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ በዛንቢያ ፕሬዚዳንት ኤዲጋርድ ሊንጉ ምሕረት ተደርጎላቸዋል።
ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም አማካኝነት በበጎፈቃደኝነት ሃሙስ እለት ከዋና ከተማዋ ሉሳካ ኬኔት ካውንዳ አየር ማረፊያ መነሻቸውን በማድረግ ወደ ትውልድ አገራቸው ተሸኝተዋል። ከ147 ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ውስጥ ሁለቱ ሴቶች መሆናቸውን (IOM) ጠቅሶ አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል

No comments:

Post a Comment

wanted officials