የዚህ አይሮፕላን ፎቶ የተወሰደው ከፋይል ነው
የበረራ ቁጥሩ 501 የሆነው የኢትዮጵያ የመንገደኞች አይሮፕላን ዛሬ ጧት ከዋሽንግተን ዲሲ በ11.30NT ሰዓት ተነስቶ ወደአዲስ አበባ በመብረር ላይ እንዳለ በተፈጠረ አስቸኳይ የጤንነት ችግር በረራው በምስራቃዊ ካናዳ ወደሚገኘው ሴይንትጆን ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ተዛዉሮ በ 4 P.M NT ማረፉን የሴይንት ጆን ቃል አቀባይ ኤሪካ ኬላንድን ጠቅሶ (Erika Kelland) የካናዳ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (CBC News) ዘገበ።
በአጋጠመው የጤንነት አስቸኳይነት ምክንያት 13 ሰዓት የሚወስደዉን በረራ አቋርጦ ከተጠቀሰው የዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ በሰላም ከማረፉ በስተቀር የጤንነቱ ችግር ምን እንደሆነና በማን ላይ እንደሆነ እንደዚሁም ለስንት ጊዜም እንደሚቆይ የምታዉቀው ነገር እንደሌለ መግለጿን ጨምሮ ዜናው ዘግቧል።
አባይ ሚዲያ ዜና በብርሃኑ
No comments:
Post a Comment