Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, January 16, 2017

የአሜሪካን ሴነተር መሪ ሚች ማክኮኔል የኢትዮጵያ የሰበአዊ መብትና የዴሞክራሲ ኣያያዝ ያሳስበኛል አሉ

የአሜሪካን ሴነተር መሪ ሚች ማክኮኔል የኢትዮጵያ የሰበአዊ መብትና የዴሞክራሲ ኣያያዝ ያሳስበኛል ሲሉ በኮሎራዶ ለሚገኙ ኢትዮጰያውያን በጻፉት ድብዳቤ ገልጸዋል:: በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን የምታደርጉትን እንቅስቃሴ በቅርበት እከታተላለሁ ብለዋል።
UNITED STATES - MAY 21: Senate Minority Leader Mitch McConnell, R-Ky., conducts a news conference in the Capitol after the senate luncheons where he addressed issues including the Oklahoma tornado. (Photo By Tom Williams/CQ Roll Call)
UNITED STATES – MAY 21: Senate Minority Leader Mitch McConnell, R-Ky., conducts a news conference in the Capitol after the senate luncheons where he addressed issues including the Oklahoma tornado. (Photo By Tom Williams/CQ Roll Call)
ባለፈው በ114ኛው የአሜሪካን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ጉዳይ በሪዞሊሽን Resolution  432 በሴነተር ቤን ካርደን ቀርቦ በጁን 28, 2016  በውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ አንዲታይ ተሞክሮ በኮሎራዶው ኮንግረስማን ማይክ ኮፍመን ተሻሽሎ የቀረበው በእንጥልጥል ላይ አንደሚገኝ ኣስታውሰዋል::
ይህን ጉዳይ  በአዲሱ የትራምፕ አስተዳደር በ115ኛው የአሜሪካን ኮንግረስ ኢትዮጵያን በሚመለከተው የሰበአዊና የዲሞክራሲ መብት ኣያያዝ ጉዳይ ላይ ህጉ ኣልፎ ተገባራዊ እንደሚሆን ምኞታቸው እንደሆነ ኣስታውቀዋል።
ለዚህ መሳካት ኢትዮጵያውያን በየስቴቱ ድጋፍ ማድረግ እንደሚኖርባቸው በማሳሰብ  ጉዳይ ትኩረት አንዲያገኝ ላድረጋችሁት እንቅስቃሴ ምስጋናችን ከፍተኛ ነው ሲሉ በደብዳቢያቸው ላይ ኣስፍረዋል::
ኢትዮጵያውያን በኮሎራዶ ነዋሪዎች ለማጆሪቲ መሪው ባለፈው አመት የአሜሪካን መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርግ ደብዳቤ መላካቸውና ከሴነተሮቻቸውና ተወካዮቻቸው ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው

ሚች ማክኮኔል  የኬንታኪ ሴኔተር ሲሆኑ ሪፐበሊካን በ2014 የሴነት ምክርቤትን ሪፐብሊካ አሸንፈው ከተቆጣጠሩ ጀምሮ የአሜሪካን ሴኔት ማጆሪቲ መሪ ሆነው በመመረጥ እያገለገሉ ያሉ ሲሆን: አሁንም በድጋሚ በመመረጥ የሪፐብሊካን ከፍተኛ አመራር የሴኔት ማጆሪቲ መሪ ናቸው::

No comments:

Post a Comment

wanted officials