Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 22, 2017

ቻይና የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅትን ለመግዛት እየተደራደረች ነው | DW



(DW) የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ አክሲዮን ማሕበር፤ የባሕርና ትራንዚት አገልግሎት እና የደረቅ ወደብ አልግሎት ድርጅቶች ተዋሕደው የተቋቋመ ነው። ድርጅቱ የገበያም ሆነ የኪሳራ ችግር ያለበት አይመስልም። ባለፈው የበጀት ዓመት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አዲስ ፎርቹን የተሰኘው የቢዝነስ እና ኤኮኖሚ ጋዜጣ ዘግቦ ነበር። ወደ 260 መዳረሻዎች አስራ አንድ መርከቦች እና 400 ተሽከርካሪዎች የሚያስተዳድረው ተቋም የተቋቋመው በጎርጎሮሳዊው 1964 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መንግሥት እና ታሩንስ ኢንቨስትመንት በተሰኘ የዩናይትድ ስቴትስ ኩባንያ ጥምረት ነበር። ከሦስት አመታት በኋላ ንጉሣዊው መንግሥት የታሩንስ ኢንቨስትመንት ኩባንያን 51 በመቶ ድርሻ በመግዛት ጠቅልሎታል። ሙሉውን ያድምጡት::

ከተመሰረተ ከ50 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው እና ለአገሪቱ የሎጂስቲክስ አገልግሎት በብቸኝነት የሚያቀርበው ተቋም ላይ የተወሰነው ውሳኔ በበርካቶች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials