Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, January 27, 2017

ለአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነት 5 አባል ሃገራት ተፎካካሪ ሆነው መቅረባቸው ተገለጸ


የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ልዩ የመሪዎች ጉባዔ አምስት አባል ሃገራት ቀጣዩ የኮሚሽኑን ሊቀመንበርነት ቦታ ለመያዝ ተፎካካሪ ሆነው መቅረባቸው ተገለጸ።
ከ54 አባል ሃገራት የሚወከሉ ፕሬዚደንቶች እንዲሁም የሃገራት ተወካዮች ከአምስቱ ተፎካካሪዎች መካከል አዲሱን ሊቀመንበር ለመምረጥ ከሰኞ ጀምሮ ድምፅ የመስጠት ሰነስርዓት እንደሚያካሄዱ ህብረቱ አስታውቋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በሃምሌ ወር በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ባካሄደው ልዩ ጉባዔ የህብረቱን ሊቀመንበር ለመምረጥ የድምፅ መስጠት ሂደትን ቢያከናውንም አንድም ተፎካካሪ ሁለት ሶስተኛ የአባል ሃገራት ድምፅ ሊያገኙ ባለመቻላቸው ምርጫው ወደ አዲስ አበባ ጉባዔ እንዲተላለፍ መደረጉ ይታወሳል።
የኢኳቶሪያል ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አጋፒቶ ሞባ-ሞኩይ እንዲሁም ሃገራቸውን ጨምሮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሲያገለግሉ የነበሩት ሴኔጋላዊው ዶ/ር አብዱላዩ ባዚልይ አምስቱ እጩዎች መሆናቸው ተመልክቷል።
የህብረቱ አባል ሃገራት በፈረንሳይኛኛ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሃገራት በመከፋፈል የሚሰጡት ድምፅ የእጩ ተወዳዳሪዎችን ለመለየት በሚደረገው ጥረት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩንም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት ይገልጻሉ።
ህብረቱን ላለፉት አምስት አመታት ያገለገሉት ተሰናባቿ ደቡብ አፍርካዊት ንኮሳንዛ ድላሚኒ ዙማ በሃገራቸው ፕረኢዚደንታዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ እቅድ በመያዛቸው በድጋሚ ለሊቀመንበርነት መወዳደር እንዳማይፈልጉ መግለጻቸውን ለመረዳት ተችሏል።
ለህብረቱ ልዩ የመሪዎች ጉባዔ ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ካሉ የሃገራት መሪዎች በተጨማሪ የአፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቅድመ የመሪዎች ጉባዔን እያካሄዱ እንደሆነም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስታውቋል።
አህጉራዊ የጸጥታና የደህንነት ጉዳዮች በዚሁ ልዩ የመሪዎች ጉባዔ መወያያ ሆነው የሚቀርቡ ሲሆነ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉባዔው በተሳካ መልኩ እንዲካሄድ የጸጥታ ቁጥጥሩ መጠናከሩን ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials