Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 19, 2017

በኢትዮጵያ ዳግም የከፋ የድርቅ አደጋ መጋረጡ ተነገረ

የወያኔ ስርዓት ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ጀምሮ ከ5 ያላነሱ ከባድ ርሃቦች ተከስተዋል ሆኖም ግን በምዕራባውያን ከለላ ምክንያት እስከ ዛሬ ገበናቸው እየተሸፈነ ቆይቷል።
ካላፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ  እየባሰበት የመጣው የረሃብ ጉዳይ  ሃገሪቱ በምግብ ምርት ራስን ለመቻል እያደረገች ባለው ጥረት ላይ ስጋት አሳድሮ እንደሚገኝ እየተነገረ ሲሆን ዘንድሮ በድጋሚ በምስራቅ በምዕራብ እና አንዳንድ የሰሜኑ ክፍሎች የርሃብተኛው ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፤ በተለይ በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ኦጋዴን አካባቢ አሳሳቢ የረሃብ አደጋ እያንዣበበ ይገኛል ተብሏል ።
በኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ አፋርና ደቡብ ክልሎች ስር በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ውስጥ የተከሰተው የድርቅ አደጋ ባለፉት ጥቂት ወራቶች ብቻ በብዙ ሺዎች የሚቆጠር የቤት እንስሶች ህይወት የቀጠፈ ሲሆን፣ ድርቁ አፋጣኝ ርብርብ ካልተደረገላት የከፋ ጉዳት ያስከትላል ተብሎ ተሰግቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የረሃቡን አደጋ ከወዲሁ ለመከላከል በአገሪቷ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንቅፋት እየሆነ እንዳለና ተረጂዎች በጊዜው እርዳታ ለማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያት ለከፍተኛ የጤና መቃወስና ለሞት አደጋ ተጋልጠው ይገኛሉ። አንዳንዶቹም አቅም ያላቸው አካባቢያቸውንና ቀዬአቸውን ለቀው ለመውጣት ቢሞክሩም አሁን በአገሪቷ ያለው ወታደራዊ አገዛዝ አካባቢውን ለቆ መሄድ ማንኛውንም እርምጃ ሊያስወስድ በመቻሉ ይህንን በመፍራት ባሉበት እንዲቀሩ ሆነዋል ።
ogaden

No comments:

Post a Comment

wanted officials