ሙሉነህ ዮሃንስ
አወን ጥንታዊው፣ ታሪከኛው፣ ፈረሰኛው አረደጃን ጊወርጊስን፤ መድሃኒአለምንና ኪዳነምህረትን ሊያነግስ ግልብጥ ብሎ የወጣው ጀግናው የዳባት ህዝብ ጥምቀትን በድጋሜ ነፃነት አውጆበታል።
በወያኔ ኮማንድ ፖስት ዘፈናቸው እንዳይሰማ የታገደባቸው አርቲስቶች…አወ ወኔ ቀስቃሽ ዜማወቻቸው ከቀን እስከምሽት የዳባትን አየር በነፃነት ሲቀዝፉት ውለዋል። የነበረው ፉከራና ሽለላ ጠላትን አርዶታል። በርሃ ቤቴ ብለው ትግል ላይ ያሉ ስመጥር ጀግኖች ሲፎከርላቸው ህዝቡ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት በቦታው የነበረውን የወያኔ ሃይል ፍርሃት ለቆበት ውሏል። ስትመቱን እንጠብቃለን ስትነኩን መጠጊያ አለን በማለት ህዝቡ የማያወላውል ለነፃነት ያለውን አቋሙን በድጋሜ አስረግጦ አስተላልፏል።

ቅድመ ወያኔ የወገራ አውራጃ ዋና ከተማ የነበረችው ዳባት ሁመራ፣ ወልቃይትና ጠገዴ በስሯ ነበር የሚተዳደሩት። ከ1977 ጀምሮ እስከ 1983 የጦር አውድማ የነበረችው ዳባት የወያኔ ከባድ የበቀል በትር የደረሰባት ታሪካዊ ከተማ ናት። በጣሊያንም ጊዜ የአርበኞች መፍለቂያ የሆነችው የእኛዋ ውብ ከተማ ጉልላቷ የሆነው አረፈጃን ጊዮርጊስ ጣልያን ቦምብ ቢጥልበትም በተአምር ሳይፈነዳ ለታሪክ ተቀምጧል። የስመ ገናናው የራስ አያሌው አገር ዳባት የጎንደር አብዮት እምብርት ነች!
የወልቃይት ጥያቄ ባለቤት ነች!
ወያኔ ለዘለአለም እንዳይመለስ ሆኖ ወደ ተዳፋቱ!
ወደ ቁልቁለቱ!
ወደ ጥልቁ የሚሸኝባት ነች!
ዳባት ውስጤ ናት! እረ ባረደጃኑ!
ወያኔ ለዘለአለም እንዳይመለስ ሆኖ ወደ ተዳፋቱ!
ወደ ቁልቁለቱ!
ወደ ጥልቁ የሚሸኝባት ነች!
ዳባት ውስጤ ናት! እረ ባረደጃኑ!
No comments:
Post a Comment