Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, January 14, 2017

"ጎንደር ሰላም የለም | አፈሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል | በርካታ ሰራዊት የጫኑ ወታደሮች ወደ ጎንደር እየገቡ ነው

"ጎንደር ሰላም የለም | አፈሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል | በርካታ ሰራዊት የጫኑ ወታደሮች
ወደ ጎንደር እየገቡ ነው 


ጎንደር በውጥረት ውስጥ ናት:: በሕወሓት መንግስት የዘር ማጥፋት ታውጆባታል:: የታሰሩ ዋና
ዋና አክቲቭስቶችም በድብቅ ከጎንደር ተጭነው ወደ አዲስ አበባ ማስቃያዎች እየተወሰዱ ነው::
ሕዝቡ ግን ከነሙሉ ልቡ የሕወሓትን መንግስት ለመፋለም ቆርጦ እንደተነሳ ነው::” ይላሉ ዘ-
ሐበሻ ያነጋገረቻቸው የጎንደር ነዋሪ ምንጫችን::
ሰሞኑን የነበረው አፈና ቀጥሎ በመዋል በዛሬው ዕለት በጎንደር የመንግስት መስሪያ ቤትና
በግል መስሪያ ቤቶችም ተቀጥረው የሚሰሩ ወጣቶች ከስራ ገበታቸው ላይ እየታፈኑ
እየተወሰዱ ይገኛሉ:: ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል የሕወሓት መንግስት ወታደሮች እና ደህነቶች
እነዚህን ወጣቶች ከስራ ገበታቸው እየወሰዱ ወዴት እንዳደረሷቸው አይታወቅም::
የሕወሓት መንግስት የጎንደር ሕዝብን ለመፍጀትና ለመግደል ቆርጦ የተነሳ ሲሆን አንድን ሕዝብ
ጨርሶ ማጥፋት እንደማይችል ግን የታወቀ ነገር ነው:: በዛሬው ዕለት በርካታ ወታደሮችን የጫኑ
የጦር መኪኖች ጎንደር እየገቡ ሲሆን በየአደባባዩም ወታደሮችን የጫኑ መኪኖች በመዘዋወር
ሕዝቡን ለማሸበር ቢጥሩም ሕዝቡ በሙሉ ልቡ ለትግል የተነሳ መሆኑን እየገለጸ እንደሚገኝ
ምንጮቻችን ዘግበዋል::
ሰሞኑን በተከታታይ በጎንደር የቦምብ ፍንዳታዎች መድረሳቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::
ኮማንድ ፖስቱ ባወጣው መግለጫው ዘንድሮ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ጉዳት
ለማድረስ እያሴሩ ያሉ ወገኖችን እያደንኩ ነው ብሏል::
ከሰሞኑ በጎንደር የደረሰው ቦምብ አደጋዎችን በተመለከተ ኮማንድ ፖስቱ ሲናገር “የሽብር ጥቃቱ
ኮማንድ ፖስቱ በጎንደር ከተማ ጥር 11 ቀን 2009 ላይ በድምቀት በሚከበረው የጥምቀት
በዓል ላይ በሰላማዊ ህዝብ ላይ አደጋ ለማድረስ ዝግጅት ያደርጉ የነበሩና ከአሻባሪና ፀረ ሰላም
ሀይሎች ጋር ትስስር ያላቸው የወንጀል ቡድኖች ላይ ዝርዝር ጥናት በማካሄድ እርምጃ መውሰድ
በጀመረበት ወቅት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ተችሏል::” ይላል::
በሌላ በኩል ሰላማዊው ሕዝብ የሕወሓት መንግስት እንደለመደው ራሱ ቦምብ አፈንድቶ
በጎንደር ሕዝብ ላይ ለማሳበብና ለማሸማቅ እንዲሁም የመብት ጥያቄውን ለዓለም አቀፉ
ማህበረሰብ የሽብር ለማስመስል እያሴረ መሆኑን ይናገራል:: በጎንደር ምንም ዓይነት መረጋጋት
የለም:

No comments:

Post a Comment

wanted officials