የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በአርባ ምንጭና አከባቢዋ በርከት ያሉ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች አመራሮችና አባላት በእስር ቤት በአስከፊ ሁኔታ እንዳሉ እየተዘገበ ይገኛል።
በአርባ ምንጭ አካባቢ ባሳለፍነው አመት አገዛዙ ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጋር ሶስት ቀናት የቆየ መጠነ ሰፊ ጦርነት ማድረጉ ይታወሳል።
በዚህ የጎሬላ ስልት ጦርነት ወያኔ በርካታ የአርበኞች ግንቦት 7 ግንባር ወታደሮችን እንደማረከና የተወሰኑትን እንደገደለ አሳውቋል።
በአንጻሩ የአርበኞች ግንቦት 7 ግንባር ወደ 20 የሚቆጠሩ የወያኔ ሰራዊትን ገድያለው ከግንባሩም የተወሰኑ በጦርነቱ እጥቻለው ሲል ተደምጧል። ነገር ግን በጦርነቱ የተሰዉት በቁጥር ስንት እንደሆኑ አላሳወቀም።
ከዚህ ጥቃት በሃላ አገዛዙ በአርባ ምንጭና በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ የተቋዋሚ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ስለላና ቁጥጥር ሲያደርግ ቆይቷል። የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም በቁጥር ከ75 በላይ የሚደርሱ በአከባቢው አገዛዙን በመቋወም የሚንቀሳቀሱ አመራሮችን ወያኔ ለእስር ዳርጓቸዋል።
በቅርቡ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሲዳማና በአርባምንጭ ታስረው የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች አመራሮች በሽብርተኝነትና አገዛዙ በሽብርተኛ ከፈረጃቸው ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ፈጥረዋል በሚል ክስ ተወንጅለዋል።
የደህንነት ሰዎች ከኮምፒዩተር ባለሙያዎች ጋር በመሆን በእስር የሚገኙ የፓለቲካ ድርጅቶች አመራሮችን የግል ኮምፒውተር በመበርበርና ፋይሎችን በመስረቅ ለክሱ እንደመረጃ ለማቅረብ እንደተዘጋጁ እስረኞቹ በደብዳቤ ባቀረቡት የቅሬታ አቤቱታ ለማወቅ ተችሏል።
በተጨማሪም እነዚህ ባለሙያዎች በእስረኞቹ የግል ኮምፒውተሮች ላይ ውንጀላውን የሚያጠናክር መረጃዎችን በመጫን በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋር ቁርኝነት እንዳላቸው አድርገው ለማሳየት እየሞከሩ እንደሆነም ከእስረኞቹ ቅሬታ መረዳት ተችሏል።
እስረኞቹ ቅሬታቸውን በጻፉት ደብዳቤ ቢያሳውቁም ከአገዛዙ የብቀላ በትር የመዳን ተስፋቸው ግን እጅግ የመነመነ እንደሆነ ይገመታል።
No comments:
Post a Comment