Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 26, 2017

ኢትዮጵያ በአለማችን ሙስና በመባባስ ላይ ካሉባቸው ሃገራት ተርታ አንዷ ሆና መፈረጃ ተመለከተ

ኢትዮጵያ በአለማችን ሙስና በመባባስ ላይ ካሉባቸው ሃገራት ተርታ አንዷ ሆና መፈረጃ ተመለከተ


ኢትዮጵያ በአለማችን ሙስና በመባባስ ላይ ካሉባቸው ሃገራት ተርታ አንዷ ሆና መፈረጃን በጉዳዩ ዙሪያ የ2016 አም ጥናቱን ይፋ ያደረገው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ገለጸ።
በ176 ሃገራት ላይ የተለያዩ መስፈርቶችን ዋቢ በማድረግ ጥናቱን ያካሄደው አለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ ከ176 የአለማችን ሃገራት መካከል በ108ኛ ደረጃ ላይ መፈረጇን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ በድርጅቱ ከተቀመጠው 100 ነጥብ መካከል 34 ነጥብን ብቻ በማግኘት በአለማችን ሙስና ከተንሰራፋባቸው ሃገራት ተርታ መቀመጧን ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በሪፖርቱ አስቀምጧል።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሰሜን ኮሪያ፣ እና ሶሪያ በአለማችን ሙስና ከተንሰራፋባቸው ሃገራት መካከል አነስተኛ ነጥብ በማግኘት ግንባር ቀደም ሆነው ተፈርጀዋል።
የተመጣጠነ የሃብት ክፍፍል አለመኖር፣ በባለስልጣናት ዘንድ የሚፈጽሙ ህገወጥ ድርጊቶችን፣ የህዝብ ሃብትን በአግባቡ አለመጠቀምና ተጓዳኝ ጉዳዮች ሙስና እንዲስፋፉ አስተዋጽዖን ያደርጋሉ ተብለው ከተቀመጡ ምክንያቶች መካከል ዋነኞቹ ሆነው ተቀምጠዋል።
ዴንማርክ፣ ኒው ዚላንድ፣ ፊንላንድ፣ 90 ከ100 ነጥብን በማግኘት ጥናቱ ከተካሄደባቸው 176 ሃገራት መካከል የተሻሉ ተብለው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ያለውን ቦታ ለመያዝ ችለዋል።
አሜሪካ 74 ነጥብን በማግኘት በ18ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፣ ሃገሪቱ ከአራት አመት በፊት 73 ነጥብን አግኝታ እንደነበር ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በአመታዊ ሪፖርቱ አመልክቷል።
በአፍሪካ ህብረት የተቋቋመ አንድ ቡድን ባለፈው አመት ይፋ ባደረገው አለም አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ ከፍተኛ ገንዘብ ወደ ውጭ ከሚወጡባቸው 10 ሃገራት መካከል አንዷ ሆና መገኘቷን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1970 እስከ 2008 አም ድረስ ሃገሪቱ 16.5 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ የሚጠጋ ገንዘብ በዚሁ ድርጊት እንዳጣች የህብረቱ አጥኚ ቡድን መረጃ የመለክታል።
ኮቲዲቯር እና ሱዳን ከኢትዮጵያ ተርታ የተፈረጁ ሲሆን፣ ናይጀሪያ፣ ግብፅ፣ እና ደቡብ አፍሪካም በየአመቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪን በዚሁ ህገወጥ ድርጊት እንዲያጡ ለመረዳት ተችላል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials