Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, January 28, 2017

የሰሜን ጎንደር አርሶ አደርና ማህበረሰብ ለወያኔ ግብር ባለመገበር ተቃውሞውን እያካሄደ ነው

የሰሜን ጎንደር አርሶ አደርና ማህበረሰብ ለወያኔ ግብር ባለመገበር ተቃውሞውን እያካሄደ ነው። ልጆቻችንና ህዝባችንን እየገደለ ያለው የወያኔ ጨቋኝ ስርዓት እኛ እየሰጠነውና እየከፈልን ባለው ግብር ስለሆነ ለዚህ አፋኝና ገዳይ ስርዓት እንዲሁም ላልመረጥነውና ለማይወክለን መንግስት  ግብር አንከፍልም እንዳሉ ተነግሯል።
የሰሜን ጎንደር የደጋውም ሆነ የቆላው ህብረተሰብ የወያኔን ስርዓት ለመጣል ከፍተኛ ትግል እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል በዚህም ትግል የወያኔ መንግስት እያደረሰብን ያለው ግፍ ከኛው በሚሰበስበው ገንዘብ መሳርያ በመግዛት ነውና ለዚህ ፋሺስት ስርዓት የኢትዮዽያ ህዝብ ግብር ባለመገበር ተቃውሞውን እንዲያደርግም የጠየቁ ሲሆን ልጆቻችንን ለሚገለው ወያኔ የገቢ ምንጭ በማድረቅ የልጆቻችንን ህይወትና ሀገራችንንም እንታደግ ብለዋል።
ፋሺስቱ የወያኔ ስርዓትም ይህን የሰሜን ጎንደር የትግል ስልት ለመቀልበስ በየወረዳው ስብሰባ የጠራ ቢሆንም ከከሀዲ የብአዴን አባላት በስተቀር ማንም ሳይገኙ በመቅረታቸው በየቤቱ በግድ የማስገበር እንቅስቃሴ መጀመሩም ተነግሯል።
በዚህም ድርጊት ከዳባት ወጣ ብሎ ባለ አንድ የገጠር ቀበሌ ግብር ክፈሉ ብለው የወረዳው የወያኔ ቅጥረኞች አንድ ስሙን ለጊዜው የማንጠቅሰው ገበሬ የገደሉ ሲሆን በዚህ የተበሳጩ ገበሬዎችም አንዱን ቅጥረኛ የብአዴን አባል ገለው  አምስቱን በማቁሰል መሳርያቸውን በመውሰድ የነፃነት ሀይሎችን መቀላቀላቸው ተነግሯል። 

No comments:

Post a Comment

wanted officials