አንድ የግብጽ ከፍተኛ ባለስልጣን እራሱን ማጥፋቱ ተሰማ። ዋህሊ ሻላቢ በመባል የሚታወቁት ሟች ስራቸውን እስከ ለቀቁበት እስከ ባለፈው እሁድ ድረስ የቀድሞ የግብጽ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን ወይም ጸሃፊ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ዋህሊ ሻላቢ ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው የለቀቁት ጋማል አል ዲን የሚባሉ ሌላ ከፍተኛ የግብጽ ባለስልጣን በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ እንደሆነም ሪፓርቶች ያሳያሉ። ዋህሊ ሻላቢ በሙስና ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ ይገኙ እንደነበረ ታውቋል።
የሁለቱ ባለስልጣን እስራት ከሙሰኝነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ አቃቢ ህጉ ተናግራል። ጋማል አል ዲን በሚሊዮን የግብጸ ፓውንድ የሚገመት ሙስና ወይም ጉቦ ተቀብለዋል በሚል ክስ ለእስር መዳረጋቸውን ከሪፖርቶች መረዳት ተችላል።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ዋህሊ ሻላቢ በክልሉ ምክር ቤት ውስጥ ከማገልገላቸውም በተጨማሪ የአገሪቱ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቶች ምክትል የፍትህ ባለስልጣንም በመሆንም ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
እንደ የዋህሊ ሻላቢ ጠበቃ ሟቹ ባለስልጣን ሲጠቀሙበት በነበረው የአንገት እስካርፍ እራሳቸውን አንቀው እንደገደሉ መረዳት ተችላል።
ጠበቃው በማከልም ዋህሊ ሻላቢ ለተከታታይ አርባ (40) ሰአታት ምርመራ ሲደረግባቸው እንደነበረና በቂ እረፍትና እንቅልፍ እንዳያገኙ ተከልክለው ነበር በማለት በግብጸ ለሚታተመው ዴይሊ ኒውስ ጋዜጣ ገልጻል። በዚህ ምክንያት ደንበኛቸው በፍተኛ ስነ ልቦና ቀውስ እንደወደቁ ጠበቃው አብራርቷል።
መንግስታዊ ያልሆኑ የውጭ ድርጅቶች በግብጸ እጅግ የከረፋ የሙስና ችግር እንደተሰናፋ በተደጋጋሚ አሳውቀዋል። በ2015 በተደረገ ጥናት ግብጸ በሙስና ከተፈረጁ 168 አገራት 88ኛደረጃ ይዛለች።
No comments:
Post a Comment