Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 11, 2017

በቡድን ተደራጅተው ከአነስተኛ እና ጥቃቅን ብድር ተቋማት ገንዘብ እንዲበደሩ የተደረጉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ያለባቸውን የብድር ገንዘብ በአስቸኳይ እንዲከፍሉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተላለፈ


በአዲስ አበባ ከተማ  ዉስጥ በሚገኙት 117 ወረዳዎች ዉስጥ የሚኖሩ እና በመንግሥት ትዕዛዝ ከአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት፤በግል እና በመደራጀት ብድር እንዲወስዱ ተደርገው የነበሩ ነዋሪዎች፤ ተበድረዉ የነበሩትን ገንዘብ በሙሉ በአስቸኳይ እንዲከፍሉ የኢህአደግ መንግሥት መመሪያ መስጠቱን ምንጮቻችን ገልጹ። ለትንሳኤ ዝግጅት ክፍል ዜናውን ያቀበሉ ምንጮች እንደሚናገሩት ለፖለቲካ ትርፍ ተብሎ ያለምንም ጥናትና ዕቅድ ብድር እንዲሰጣቸው ተደረገው የነበሩ እነዚህ ተበዳሪዎች የተበደሩትን ገንዘብ መክፈል መጀመር የነበረባቸው ከአመትና ሁለት አመት በፊት የነበረ ቢሆንም በገጠማቸው የተለያየ ኪሳራ ምክንያት እስከዛሬ ለመክፈል ሳይችሉ ቀርተዋል።
ተበዳሪዎች ያለምንም ማስጠንቀቂያና የጊዜ ገደብ በድንገት ያለባቸውን ገንዘብ በአስቸኳይ  እንዲከፈሉ መመሪያ የተላለፈበት ምክንያት በውል አልተገለጸም። ሆኖም አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይህንን ድንገተኛ የመንግሥት መመሪያ ምናልባት በመንግሥት በኩል እንደገጠመው የሚነገረው የገንዘብ ዕጥረት እየተባባሰ መሄዱን የሚያመለክት ነው አለያም ደግሞ ተበዳሪዎች እዳተኛ መሆናቸውን እንዲያስታውሱ በማድረግ ጊዜ ጠብቆ ሊፈነዳ ይችላል ተብሎ በተሰጋው ህዝባዊ ተቃውሞ እንዳይሳተፉ ለማስጠንቀቅ እንደሆነ ይናገራሉ። 
 በአዲስ አበባ ከተማ በአነስተኛና ጥቃቅን ንግዶች ለመሠማራት በግልና በቡድን ተደራጅተው ብድር እንዲወስዱ ከተደረጉት ግለሰቦች አብዛኛዎቹ  ብድሩን የወሰዱት በቀበሌ ካድሬዎች ጉትጎታታ እንደሆነና ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን የሚሰሩበትን ቦታ እንደሚሰጣቸዉ ቃል ተገብቶላቸው እንደነበረ ይገልጻሉ። ነገርግን ገንዘቡን ተበድረው  ወደስራ ከተሰማሩ በሗላ የተበደሩት ገንዘብ መጠን እና የተሰጣቸዉ የንግድ ምድብ የማይጣጣም እንደሆነ በዚህም የተነሳ ለኪሳራ በመዳረጋቸው ብድሩን ከወሰዱት መሀል 5 ፐርሰንት የሚያህሉት እንኳን ሊከፍሉ ይችላሉ ተብሎ እንደማይገመት ይገለጻል።
ገንዘቡን ከወሰዱ ቦኋላ የተሰወሩና የት እንደገቡ የማይታወቅ ሰዎች ቁጥርም ቀላል እንዳልሆነ ይነገራል።  የኢህአደግ መንግስት በተለይም ወጣቱን በአነስተኛ እና ጥቃቅን ንግድ ቡድን  በማደራጀት እራሳቸውን እንዲችሉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጌያለሁ በማለት ርካሽ ፕሮፖጋንዳ ሲነዛ በሌላ በኩል ደግሞ የገንዘብ ብድር ለማግኘት በቡድን ተደራጁ የተባሉትን በአባልነት ካልተመዘገባችሁ እያለ ያለውደታቸው የአባልነት ፎርም እንዲሞሉ ሲያስገድዳቸው እንደኖረ በምሬት የሚናገሩ ሰዎች በርካታ ናቸው ። “እኛ የተበደርነውን ገንዘብ ሠርተን እንከፍላችኋለን እንጂ ያለውዴታችን  የአባልነት ፎርም አንሞላም” ብለው ያንገራገሩትን ወጣቶች ወይም ተበዳሪዎችን  “ከአሸባሪዎች ጋር  ግንኙነት ስላላችሁ ነዉ” በማለት እየወነጀለ ለእስር እና ለእንግልት እንደዳረጋቸውም መረጃውን ያቀበሉን ምንጮች ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials