Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 22, 2017

በመንገዱ ፣,,, የማለዳ ወግ…ዱባይ ማራቶን፣ ባንዴራውና ቅስም ሰባረው ፖለቲካ ! – ነቢዩ ሲራክ



* ዱባይ ላይ ፈተና ውስጥ የወደቀችው ጀግና አትሌት ወርቅነሽ …
በዱባይ 2017 ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ ሀገሯን ወክላ ሮጣ ተሯሩጣ አሸንፋ እንደገባች ቅስምን ሰባሪ ምርጫ ገጠማት ፣ ሁለት ባንዴራ ! ቅስም ሰባረውን ፖለቲካ ትርክት ለመታዘብና ለመቁሰል ጀግናዋ አትሌት ወርቅነሽ መመልከት በቂ ነው ! …
አዎ ጀግናዋ አትሌት በድል አሸንፋ ገባች ፣ ደስታዋን እየዞረች ስትገልጽ ከደጋፊ የሀገር ልጆች ባንዴራ ተወረወረላት ፣ ረመድ ብላ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዴረውን አነሳችው ፣ ባለ ግርማውን አርማ ላፍታ ዘርግታ ለአፍታ ደመቀችበት ! ለአፍታ አንስታ ደምቃ ከተመለከተች በኋላ ደግሞ ከራሷ ጋር ተጣላች … በቅጽበት ምልከታ የሀገርና ህዝብ ክብር አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ባንዴራዋን ከፍ ካደረገችበት አወረደችው :( አሽቀንጥራ ጣለችው :( አትሌቷ ለኩራት ድል ምክንያቷ የሆነውን ምልክቷን የፖለቲካ ፍም እሳት አደጋውን ፈርታ ክብሩ ዝንፍ የማይለውን ሰንደቅ ወረወረችው :( ሰንደቅ ባንዴራችን ከእጇ ላይ ሰብስባ ወረወረችና በቀስታ ስትራመድ እጆችዋን ወደ አይኗ ልካ ነበር ፣ በሆነው በግና እያለቀሰች ይመስለኛል ! እንዴት አያስለቅስ አያስነባ ? አትሌቷ ከታላቅ ታሪካዊ ቦታ ታሪክ መስራት የምትችልበት አጋጣሚ ብታገኝም አልመረጠችውም ! ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላንቃ ከመግባት ይልቅ ምርጫዋ ሌላ ሆነ … ምርጫ ደግሞ የራስ ነው ! …በቃ ይህው ነው !
በእኛ ዘባተሎ ፖለቲካ ፈተና ውስጥ አያለፈ ባለው ባንዴራ ምርጫ ላይ የወደቀችው እህት አሽቀንጥራ ከጣለችው ባንዴራ ስር የእኒያ ጀግኖችና ከትውልድ ትውልድ የሚዘከር የኢትዮጵያ እውነት አለበት ፣ ዳሩ ግን አዘንኩ እንጅ አልፈረድኩባትም ! ዘባተሎ ፖለቲካ ያመጣው ቆሻሻ ጫወታ ግን ለመለያየታችን ምክንያት ነውና ዛሬም አዘንኩ :(
እኔ ሲጀመር በጀግናዋ አትሌት ባዝንም አልፈፈርድባትም … ሁሉም ከፍ ባለው ሀገራዊና ወገናዊ ሞራል ይመራ ለማለት ያስቸግራል ፣ ሁሉም ከፍ ካለው ሀገራዊና ወገናዊ ሞራል ዝቅ ብሎ ማየት ደግሞ ያስከፋል :( የሀገርና የህዝብ ክብር ዝቅ ያደረገው የፖለቲካ ዘባተሎ በድል ደስታችንም ቀን ሰላም አልሰጠንም ፣ በዱባይ 2017 ማራቶን በአረንጓዴው ጎርፍ አንጸባራቂ ውጤት በድል ደምቀን እያለን ፣ በጀግናዋ አትሌትና በባንዴራው ፍጥጫ ብሎም በ ቅስም ሰባረው ፖለቲካ ያመጣብን ጣጣ እንዲህ ለያይቶ ያፏክተናል ! ይህም ያማል !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ጥር 13 ቀን 2009 ዓም

No comments:

Post a Comment

wanted officials