Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, January 10, 2017

የአላሙዲና የሌሎች ባለሃብቶች ድርጅቶችና ሆቴሎች በባህርዳር ሰራተኞችን እየቀነሱ ነው



ከአያሌው መንበር
ባህር ዳር ውስጥ ያሉ የግል ተቋማት በተለይም ሆቴሎች ሰራተኞቻቸውን እየቀነሱ ነው።ገቢ የለንም በሚል ምክንያት የእነ አላሙዲ ሪዞርትን ጨምሮ ሌሎች ስመጥር ሆቴሎች ሰሞኑን ብዙ ሰራተኞች ቀንሰዋል።
ይህ አማራውን ከስራ ውጭ በማድረግ ለዕለት እንኳን የሚበላው በማሳጣት ለህወሃት ተገዥ ይሆን ዘንድ የማጥቂያ መንገድም ነው። በርካታ የአማራ ወጣቶች በስራ አጥነት እየተሰቃዩ የቤተሰብ ሸክም በሆኑበትና አማራጭ አጥተው በህገ ወጥ መንገድ ለስደት እየተዳረጉ ባሉበት ጊዜ ታቅዶበት ቤተሰቦቻቸው ከሚያገኟት የእጅ ወደ አፍ ገቢ እንኳን ፈፅሞ ሲከለከሉ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰብ አንድ ሙሉ አዕምሮ ላለው ሰው ቀላል አይደለም።
በድሮው ስርዓት ከተገነባው የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ውጭ ሌላ ሰፊ የሰው ሀይል መሸከም የሚችል ኢንዱስትሪ የሌላት ባህር ዳር እና መላው አማራ ላለፉት ዓመታት የህወሃትን ባለስልጣናት ሆድና ኪስ የማድለቢያ ፋጉሎ ነው ሲያቀርብ የኖረው።ዛሬ ደግሞ ሀብት ንብረታቸው ሁሉ ወደ መቀሌ ሆኖ ሆቴል መገንባት ቀርቶ በሆቴሎችና ጥቃቅን ካፌዎች እንኳን ተቀጥረው እንዳይሰሩ ይኸው ገበያ የለም በሚል በርካቶች ከስራ እየተሰናበቱ ነው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials