Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, January 9, 2017

የአማራ ሃኪሞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ጋሹ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተዛወረ



ለገሠ ወ/ሃና

የአማራ ሃኪሞች ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ጋሹ ክንዱ ከባህርዳር ፓሊስ ጣቢያ አ.አ. ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እንደወሰዱት ዛሬ ታህሳስ 5/2009 ዓም እንዲጠይቁ የላኳቸው ሰዎች አረጋግጠዋል በአካል ማግኘት ባይቻልም እዛ ለመኖሩ ምርመራ ላይ ስለሆነ ማየት አትችሉም ብለው ስንቅ ተቀብለዋል::

ወጣቱ ሀኪም ዶክተር ጋሹ ክንዱ ሀሙስ ታህሳስ 27 /2009 ዓም ባህርዳር ከተማ ተይዞ እዛው ባህርዳር 9ኛ ፓሊስ ጣቢያ ከታሰረ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መቼ እንዳዛወሩት አልታወቀም ፡፡
ወጣቱ ሐኪም ዶ/ር ጋሹ ክንዱ በዩኒቨርሲት ቆይታውም የኢትዮጵያ የህክምና ተማሪዎች ማህበር ሊቀመንበር በመሆን በተለያዩ ዓለማት በመዞር ልምዱን ለሌሎች ሲያካፍልና ከሌሎች አገራት የህክምና ሙያተኞች ልምድ በመለዋወጥ አቅሙን አጎልብቷል፡፡

ዶ/ር ጋሹ በወቅቱ በነበረው ሚና ምክንያት ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገብቶ እንዲሰራ በነ ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢጠየቅ ፈቃደኛ ሣይሆን ቀርቷል የህክምና ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ቡሬ ዳሞት አጠቃላይ ሆስፒታል ተመድቦ በህክምና ሃላፊነት(ሜዲካል ዳይሬክተርነት) በማገልገል ስራውን በአግባቡ እየተወጣ ነበር፡፡ ዶ/ር ጋሹ ለበአል ወደ ቤተሰብ ሲሄድ ባህር ዳር ሄዶ እዛው ታህሳስ 27/2009 ዓም ባልታወቀ ምክንያት ታስሮ በአሉን ከቤተሰቦች ጋር ሳይሆን በእስር እንዲያሳልፍ ተገዷል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials