Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 4, 2017

የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን መፀሐፍ”የአማራና ኦሮሞ እውነተኛው የዘር ምንጭ” የተባለውን የምትተቹና የምትቃወሙ ኢትዮጵያን ባለማወቅ፣ ከቅናትና ምቀኝነት በተነሳ ሃሰት ነው።

የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን መፀሐፍ”የአማራና ኦሮሞ እውነተኛው የዘር ምንጭ” የተባለውን የምትተቹና የምትቃወሙ ኢትዮጵያን ባለማወቅ፣ ከቅናትና ምቀኝነት በተነሳ ሃሰት ነው። ከይሁነው አሰፋ

አስተያየትና መተቸት አግባብ ያለው ተመክሮ ሆኖ ሳለ በተለይ ሶስት ስዎች የተቻችሁትና ያቀረባችሁ ነቀፌታ ከእውነትና ሃቅ እጅግ የራቀ ከመሆን ጋር ከቅናትና ምቀኝነት የተነሳ ውሸትና ሃስትን ያካተተ ለመሆኑ በጉልህ አሳይቶባችኋል።እውነትን ፈላጊ ትክክለኛ ነገሮችን የሚሻ፣እንዲሁም የተማርንና አወቅን ከሚሉ፣እኩል የትምህርት ችሎታና ማዕረግ፣ ኢትዮጵያንና ታሪኳንም እናውቃለን ከምትሉ በተለይ ከፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌና ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚልክያስ በመጸሃፉ ላይ የሰነዘራችሁት አስተያየት እጅግ በጣም ዝቅ ያለ ትምህርታዊ ተመክሮን፣ክብርና ማዕረግን ያልተከተለ ሥነ-ምግባርና ፕሮፌሽናሊዝምን ያጓደለ ነው።ከዚህም የተነሳ የሰነዘራችሁት ትችት፣አስተያየትና ተቃውሞ ትምህርታዊ እርማትን የሚያመጣ ሳይሆን አሉባልታና ተራ ነቀፌታ፣ ቅናትና ተንኰልን የሚያንጸባርቅ በመሆኑ ለብዙ ታዛቢዎች ዘንድ ቅሬታንና ሃዘንን አሳድሮብናል።

 ለፕሮፌሰር ጌታቸውን ትችትና ነቀፌታ በተመለከተ እራሱ ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በሰፊውና አግባብ የሆነውን መልስ ሰሞኑን ሰለሰጠበት እኔ በዚህ ላይ ብዙ አልልም። ይህን ጉዳይ የተከታተላችሁ ትረዱት አላችሁ ብየ እገምታለሁ።ነገር ግን ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ በተደጋጋሚ ብዙ ጊዜ የሚሰጧቸው አስተያያቶች እጅግ የተሳሳቱ፣ ግራ የሚያጋቡና ከእኝህ ፕሮፌሰር ነኝ ከሚሉ የሚጠበቁና ትምህርት የሚሰጡ ሆነው አይታዮም።ከእውነት የራቁና ፈር የለቀቁ፣ መፍትሄ እማይሆኑ አስተያየቶችና አሳቦች ናቸው።ለምሳሌ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ልጥቁስ፤1ኛ/ ከዚህ ከአሁኑ ጉዳይ ብጀምር፣ይህ መጸሃፍ ከ45- 63 ቢብሊወግራፎች ከነ ገጻቸው እያጠቀሰና የጥንታዊ መጸሃፍት ግኝት ከሆነው እያቀናበረ የጻፈውን ተረት ተረት ነው ብሎ፣ ብርቅየ የኢትዮጵያን የቤተክርስቱያንና የሕዝቧን ታሪክ ማናናቅና ለማራከስ መሞከር።ይህን መጸሃፍ ብቻ ሳይሆን እየነቀፉ ያሉት ሬፈራንሶችንና ከአምሳ አመት በፊት በመሪራስ አማን በላይ የተገኘውን ማስረጃና እውነተኛ ታሪክነቱ ተረጋግጦ ተመዝግቦ በታሪክ ሰነድነቱ የተቀመጠውን ጭምር ነው።

 2ኛ/ ከባንዳው ወያኔ ጋር ያለውን ትግላችንን “ወያኔን የተቃወመውን ሁሉ ደግፉ ብለው” ትግላችን ከባንዳውና ከተገንጣ ድርጅቶች ጋር እዲተራመስ ይሰብካሉ።3ኛ/ የተደራጀና ሊመራ የሚችል ድርጅት ሳይኖር የቀረን ክተት ነው ብለው ቅስቀሳ ጀምረው ነበር። ሌሎች ብዙ ማሳሳቻዎችን በየጊዜው ይሰጣሉ በውጭ ያለውን ሰደተኛ ሕዝብ ያሳስታሉ።ይህን ህዝብ የሚያቀው ሲሆን በአጠቃላይ ከፕሮፌሰሩ የሚጠበቅ ትምህርት ሰጭና የምንከተለው አስተያየት የተዛባ ነው።

 ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚልኪያስ ያቀረበው ትችትና ነቀፌታ የመሰለ ተቃውሞ አዘል ነው። በጠቅላላው አሳቡና የሰነዘረው አስተያየት ሲገመግም ፣ ለምን ፕሮፌሰር ፍቅሬ ኢትዮጵያን በተመለከተ፣ የህዝብን ስሜትና ቀልብ የሚስብና ተወዳጅ መጸሀፍ ጻፈ ብሎ ቅናት ያለበት መስሎ ከመታየቱም በላይ ተበለጥኩ ብሎ የተናደደ ይመስላል እንጂ የመጸሃፉን ስህተት ወይም ሶርሱን ጠቅሶ ለአንባቢና ለጽሃፊው ትምህርታዊ እርማት እንዲያገኝ የሰጠው ማሳሰቢያነት የለም። መጸሃፍ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት በመነበብ ላይ ያለና ህዝቡን በኢትዮጵያዊነቱ እጅግ እያቀራረበው ነው። ከዚህም የተነሳ ወያኔ እገበያ ላይ እንዳይውል ከልክሎታል።

 በሶስተኛ ደረጃ ተችና ተቃዋሚ ሆኖ የቀረበው ምትኩ አዲስ ተብየው ሲሆን መጸሃፍን “ልብ ወለድ “ ነው ይላል። ይህ ሰው ከተገንጣዎች ወገን የሆነ የሚናገረውና ሊያስተላልፈው የሚፈልገው የወያኔን ፀረ- ኢትዮጵያ አቋም የያዘ ዓይኑን ጨፍኖ ለመቃወም ብቻ የተነሳና የተላከ ግብዝ ሰው ነው። ኢትዮጵያና ህዝቧን አይደለም እራሱን እኔ ማነኝ ብሎ በመጠየቅ ያወቀና የተረዳ አይደለም።ባቀረባቸው ተራና መናኛ አስተያየቶች የእራሱን ዝቅተኝነትና አለማወቅ ከማጸባረቁ ባሻገር በዚህ ድርጊቱ አዝኛለሁ።ኢትዮጵያን ያወቀውና የተረዳው ወያኔና ኦነግ በነገሩትና ባስተማሩት ነው ያየው። ለኢትዮጵያ ስም የሰጧት ግሪኮች ናቸው ብሎ ያመነ በውጭ በጠላት ወሬ የሚያምን ነው።የወያኔን ሃስትና ግልብጥ ታሪክ አፍቃሪዎች (የአኖሌን፣ ፕሮቻስካን ከፋፋይና ፀረ-ኢትዮጵያ ታሪክና ተገንጣዮች እንዲሁም አማራ የሚባል ጎሳ የለም፣ ኦሮሞ መጤ ነው፣ መሬት የለውም ቅዠት) ውስጥ የገቡና በወያኔ ርዮተ- ዓለም የሚመሩ እውነተኛው የኢትዮጵና ህዝቧ ታሪክ አይዋጥላቸውም።የዚህ ውጤቶች ናቸው እነዚህ ተችዎች።

ኢትዮጵያ ጥንታዊት፣ ረዥምና ሰፊ ታሪክ ያላት አገር ከመሆን ጋር በዓለም በቀደምትነት መንግሥት መስርተው ከኖሩት ውስጥ አንዷ እንደሆነች በብዙ የዓለም ታሪኮች ተመዝግባና ተነግሮላት እንደሆነና በሳይንስ ሊቃውንትም የሰው ልጅ መገኘትም በዚቹ ኢትዮጵያ መሆኑ የተረጋገጠና የታተመ መረጃ አለ። ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳም ይህን እያጣቀሰ ሃቁን አስቀምጦታል። ዶ/ር ፍቅሬ የጻፈው እውነት ሃቁን እኛነታችንን የሚገልጸውን ኢትዮጵያን ይቺ ናት ለማለት እንጂ ማንንም የማቀራራብ፣ ሰላምና ፍቅርን ለመፍጠር የተደረገ ልብ ወለድ አይደለም። ነው ማለትም የኢትዮጵያ ጠላቶች ተራና እርካሽ ወሬ ነው።

ስለዚህ እነዚህ ከዚህ በላይ የጠቀስኳቸው ሰዎች በዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ “የአማራና ኦሮሞ እወነተኛው የዘር ምንጭ” በተሰኘው መጸሀፍ ላይ የተሰጡት ትችትና ተቃውም ፈጽሞ ከእወት የራቀ አሉባልታና ፍሬቢስ ወሬ ስለሆነ ይህን መጸሀፍ አንብባችሁ ሃቁን የኢትዮጵያን ታሪክ በመረዳት ከየት መጣን፣ የት ነው ያለ ነው፣ወዴት ነው የምንሄደው ብለን እራሳችን እድናውቅና እዲንረዳ ጠቃሚና አሰፈላጊ ስለሆነ አንብቡትና የራሳችሁን ግምጋሜ አድርጉ እያልኩ የግሌን አስተያየት አቀርባለሁ።በመጨረሻ ለፕሮፌስር ፍቅሬ ቶሎሳ እጅግ ብዙ መጸሃፍትን አንብቦና ጨምቆ ለእትም በማብቃት የኢትዮጵያን ብርቅዬ ታሪክ ለንባብ አብቅቶ ስላስተማረን እጅግ ልባዊ አክብሮቴንና ምስጋናየን አቀርባለሁ።
ኢትዮጵያ ምንጊዜም አኩሪ ታሪክ አላት ታህሳስ 26/ 2009

No comments:

Post a Comment

wanted officials