Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 4, 2017

በመላ አማራ አካባቢ ህዝባዊ አብዮቱ እየተቀጣጠለ ነው!

ጎንደር ላይ ወያኔ በጭንቅ ውስጥ ነው!— ወያኔ የራሱን ባለስልጣናት እያሰረ ትርምስ ውስጥ ነው!
— በመላ አማራ አካባቢ ህዝባዊ አብዮቱ እየተቀጣጠለ ነው!
ሙሉነህ ዮሃንስ
በሰሜን ጎንደር የቆላማው ወገራ ገበሬዎች ለወያኔ ሰራዊት የምግብ አቅርቦት አናደርግም በማለት ስላመፁ እንኳን ሰው የቆላው አየር ንብረቱ ጭምር የተዋጋው የወያኔ ሰራዊት ከሶስት ቀን በፊት ቦታዉን ለቆ መውጣቱ ታውቋል። ነገር ግን ዱር ቤቴ ያለውን ታጋይ ህዝብ ለማዘናጋትም ሊሆን ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ ከጎበዝ አለቆች ማሳሰቢያ ተላልፏል።
የራሱን ሹሞች እንኳን ማመን የተሳነው ወያኔ እስሩን ቀጥሎበታል። የጎንደር ከተማ መዘጋጃ ቤት ሀላፊ የነበረዉ ፍቃዱ ስለመታሰሩ መረጃ ደርሶናል።
የሰሜን ጎንደር ማረሚያ ቤቶች በዉክልና ሀላፊነት ተሰጥቶት የነበረው ትዉልዱ ከወቅን 5 km ርቀት ላይ በምትገኘው የገጠር ቀበሌ የሆነው ኢንስፔክተር ሰጠኝ ሙሌ ኮ/ል ደመቀን ከአፈና ለማስጣል በነበረው ውጊያ የተሰዋውን የአርማጭሆ ስመጥር ጀግና ሲሳይ ቀብር ላይ በለቅሶ ስነ ስርዐት ወቅት ፎክረሀል በማለት ታስሯል።
ጎንደር ላይ በአዲስ መልኩ ሆን ብለዉ ሙስናን ሰበብ በማድረግ እስካሁን 8 ባለሀብቶች ሲታሰሩ ቀሪዎቹ ጎንደርን ለቀዉ እየሄዱ ነዉ። ለማሰር የታቀደው 35 የበርሃ አራሾችን መሆኑ ስለታወቀ ጥንቃቄ ይደረግ።
ወያኔ ህዝቡንም የራሷን ሰወችም በጅምላ ማሰር ላይ መሆኗ የደረሰባትን ታላቅ ውድቀት ያሳያል። በንፅፅር ደግሞ እጅግ ብዙ የጎበዝ አለቆች በመላ ጎንደር ለወያኔ በሚያስሸብር መልኩ ህዝቡን እያደራጁ ነው። ሰሞኑን በጎጃም (የመምህራን አመፅና እስር)፣ በወሎ (የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አመፅ) በሰሜን ሸዋ (የደብረ ብርሃን የዩንቨርስቲ መቃጠልና) አዳዲስ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች መስተናገዳቸው በአማራው ህዝብ በሙሉ የወያኔ መሰረት ተሸርሽሮ ማለቁን እያበሰረ ነው።
የነፃነት ጥያቄ በአፈና አይመለስም!
ህዝብ ያሸንፋል©!
ሙሉነህ ዮሃንስ

No comments:

Post a Comment

wanted officials