Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 8, 2017

ጎንደር ላይ የጥምቀት በአል በአጥቢያ ቤተክርስቲያናት ብቻ እንዲከበር ጥሪ ቀርቧል።

ጎንደር ላይ የጥምቀት በአል በአጥቢያ ቤተክርስቲያናት ብቻ እንዲከበር ጥሪ ቀርቧል።
ገዢው ፓርቲ ህዋሃት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈፀመ የሚገኘውን ኢሰብአዊ ድርጊትን ለማውገዝ ታላቅ የተቃውሞ መርሃ ግብር የተዘጋጀ ሲሆን በጎንደርና አካባቢው ወረቀቶች እየተበተኑ ይገኛሉ።
የጥምቀት በአል ጎንደር ላይ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ የጥምቀት በአልን አለማክበሩ ለህወሃት ትልቅ ኪሳራ ከመሆኑም በላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ድል ነው። በዶላር እጥረት ፍዳውን እያየ ለሚገኘው የኢትዮጵያ አምባገነናዊ መንግሥት ከቱሪስቶች ብዙ ገንዘብ እሰበስብበታለሁ ብሎ ከሚጠብቃቸው በአላት አንዱ ጥምቀት ሲሆን ይህ እንዳይሳካ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ከኢትዮጵያ ውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ቱሪስቶች ወደጎንደር እንዳይሄዱ ለአውሮፓ ሀገራትና የአሜሪካ ኤምባሲዎች የማሳሰቢያ ደብዳቤ ከአሁኑ ሰአት ጀምሮ ልንፅፍ የሚገባ ሲሆን ሐገር ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያን መልእክቱን ለመላው የአካባቢው ነዋሪዎች ልታስተላልፉ ይገባል።
ጥምቀት ጎንደር ላይ የሚከበር ከሆነ ህዋሃት ህዝቡ ሲሰበሰብ እንደኢሬቻ በአል ግርግር በማስነሳት እና ምናልባትም ቦንብ በማፈንዳት የተወሰኑ ሰዎች እንዲሞቱ በማድረግ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ፈፀሙት በማለት ከነጮቹ ደጃፍ የተለመደ ልመናውን ሊቀጥል እንደሚችል እሙን ነው። ይህ ከመሆኑ በፊት ሁላችንም ለወገኖቻችን እንድረስላቸው።
#ኤርሚያስ_ቶኩማ

No comments:

Post a Comment

wanted officials