ተዋናይ ፣ኮሜዲያን፣ አዘጋጅ ሆነ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል፡፡ በመድረክ ፣ በሬዲዩ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም ስራ እና በጋዜጠኝነት ሙያ ሠርቷል ። በአፍሪካ የመድረክ ሙያተኞች ማህበር በሊቀመንበርነት መርቷል ፣ በአትላንታ ጆርጂያ በበረከተው የሙያው ሥራ ኖቬምበር 24 ቀን በስሙ ተሰይሞለታል። (ጋሽ ደቤ) በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት ካሉት አርቲስቶች ግንባር ቀደሙና አንጋፋው ነው። ጋሽ ደቤ ከሰራቸው ስራዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ፤ ያላቻ ጋብቻ ፣ ሮሚዎባ ዡልየት ፣ ጠልፎ በኪሴ ። እንዲሁም ዘ ጌም ኦፍ ቼዝ ፣ ኦቴሎ እና አዳ ኦክ አራክል በተመልካች አድናቆትን ያተረፉ የሙሉ ጊዜ ቲያትር በእንግሊዝኛ የተወነ ድንቅ አርቲስት ነው። የበጋ ሌሊት፣ አንድ ዓመት ከአንድ ቀን ፣ እናት ዓለም ጠኑ ፣ ዋናው ተቆጣጣሪ ፣የአዘውንቶች ክበብ ፣ የወፍ ጎጆ ፣ ኪንግ ሊር ፣ የቬኒሱ ነጋዴ የተሳተፈባቸው እና ምርጥ ብቃቱን ያሳየባቸው ሥራዎች ናቸው ።
በፊልም የሙያ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሳተፈባቸው ፤ ዘ ሴይለር ፍሮም ጂብራልታር ፣ ሻፍት ኢን አፍሪካ ፣ ጉማ ፣ ዚ አፍሪካን ስፓይ፣ ዜልዳ ፣ አፍሪካ ዘግሬቭ ዲገር ፣ ዘ ግሬት ሪቤሊየን ይገኝበታል ። የአርቲስት ደበበ ስራዎች በርካታ ናቸው ፡፡ ከመድረክና ፊልም ስራዎቹ በተጨማሪ የስታንስላቭስኪ የተዋናይ ሀሁ መማሪያ መፃፍ በመተርጎም ለበርካታ አርቲስቶች የሙያቸው ፊደል መቁጠርያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ፡፡ ጋሽ ደቤ ደከመኝ የማይል ብርቱ ሰው ነው። በትርጉም በኩልም የሙሉ ጊዜ ቲያትር ፤ ያልታመመው በሽተኛ፣ ድብልቅልቅ እንዲሁም ጎርፉ የተሰኙ ቲያትሮች የተረጎመ ሲሆን ። ከመጽሐፍ የባሩድ በርሜል የእሱ የትርጉም ሥራዎች ናቸው ። የራሱን ወጥ ሥራ በተመለከተ የእምነቴ ፈተና የተሰኘ መጽሐፉ ለንባብ አብቅቷል ።
አርቲስት ደበበ በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የቴአትር ኢንሳይክሎፒዲያን አፍሪካን በመወከል የኤዲቶርያል ቦርድ አባል በመሆን አገልግለዋል ። በተጨማሪ የቲያትር ሥልጠናዎችን በየሃገራቱ እየተጋበዘ አስተምሯል ፡፡ አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ቀያይ ቀምበጦች በሚለው ፊልም ላይ ባሳየው የተዋናይነት ብቃቱ በካናዳ ቫንኩቨር የGolden Leopard Award ተሸላሚ ሆኗል።
አንጋፋ እና ተወዳጅ የሆነው #አርቲስ_ደበበ_እሸቱ ፤ የበጎ ሰው ተግባር የሆነ መልካም ሥራ በማስተባበር ለወገን ደራሽ ወገን ነው በማለት ጥሪውን እያስተላለፈ ይገኛል ። እንዲህም አለ " በጌርጌሲኖን የአእምሮ ህመምተኞች መርጃ ማህበር በሚደረገው የድረሱልን ጥሪ በመገኘት መልስ የመስጠት የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ። አለንላችሁ እንበላቸው፤ ጥሪያችሁን ሰምተን መጣን ብለን ችግራቸውን እንካፈላቸው ! የተቸገሩትን መርዳት በዓምላክ ፊት ክብርና ሞገስ ያስገኝልናል!። " በማለት ጥሪውን አስተላልፈዋል ። ለማህበሩ ገቢ ለማሰባሰብ እና ግንዛቤ ለማስጨበጥ አንደ ቀን ሙሉ በአዲስ አበባ የሰዎችን ጫማ በማፅዳት (ሊስትሮ ) በመጥረግ አርአያ ለመሆን የተቻለውን ጥረት ሲያደርግ ሰዎች ተመልክተዋል ።
#ጌርጌሲኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር። በየጎዳና ላይ ወድቀው ካለ ፈጣሪ በስተቀር አስታዋሽ አጥተው በአዕምሮ ሕመምና በተለያዩ ደዌ ተመተው ዝናብ ብርድ ረሃብና ጥሙ የሚፈራረቅባቸው ችግረኖችንና ሚስኪኖች ወገኖቻችን የሚገኙበት አነስተኛ መጠለያ ነው። ማህበሩን ለማገዝ ወገኖቻችን ለመርዳት ሁላችንም የተቻልን ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል።በገንዘብ፣በቁሳቁስ፣ በጉልበት፣በእውቀት እንዲሁም የተረጂዎችን ልብሳቸውን ፣ ሰውነታቸውን በማጠብ ፣ ምግብ በማጉረስና በመንከባከብ ፣ብርድ ልብስ፣አንሶላ የተለያዩ አልባሳት ሳሙና እና የሚያስፍልጋቸውን ሁሉ በቦታው ተገኝተው በመስጠት የተቻለን ጥረት በማድረግ የበጎነት ሥራ ለመስራት እግዚአብሔር ይርዳን ! ለማህበሩ መስራቾች እንዲሁም ማህበሩን ለማገዝ እና የማህበሩን ሥራ ለማስተዋወቅ ለምትጥሩ በሙሉ ምስጋና እንዲሁም አድናቆት ይገባችሁል። አርቲስት ደበበ እሸቱ አሁንም ፈጣሪ እድሜና ጤና ከሰው መውደድ ጋር አብዝቶ ይስጥልን፣ አሜን !!!
(ይድነቃቸው ከበደ)
No comments:
Post a Comment