Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 11, 2017

ታስረው የነበሩ ዜጎች አሰቃቂ የሆኑ የማሰቃያ ምርመራዎች እንደተካሄደባቸው እየገለጹ ነው

በወያኔ የጸጥታ ኃይሎች ታስረው በተለያዩ የማጎሪያ ጣቢያዎች የነበሩ ዜጎች በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት አሰቃቂ በደልና ስቃይ የደረሰባቸው መሆኑን እየተናገሩ ይገኛሉ። ኑሩሀሰን ሁሴን በአለም ገና ወለቴ አካባቢ በነበረው ህዝባዊ አመጽ ተሳትፈሃል ተብሎ ተይዞ ለሁለት ወር ያህል በአዋሽ ሰባት የማጎሪያ ጣቢያ ታስረው ከተሰቃዩት መካከል አንዱ ነው። ነሩሀሰን በእስር በነበረበት ጊዜ መርማሪዎቹ የሰራኸውን እመን ሌሎቹንም ጠቁም በማለት በምርመራ ያሰቃዩት መሆኑን ገልጾ ቀጫጭን ብረቶች በእጆቹ መካከል በማስገባትና እጆቹን ወደ ኋላ በማጠፍ ከማሰቃየታቸውም በላይ ከስቃይ ለማምለጥ ሲፈራገጥ አንዱን መርመራሪ በእግሩ በመምታቱ የነበሩት ሁሉ በዱላ በመቀጥቀጥ ተረባርበውበት ሰውነቱን እንዳሽመደመዱት ገልጿል። ሰውነቱ በመጎዳቱ መጠነኛ ህክምና ቢደረግለትም በሌሎች እስረኞች በመታገዝ እየተንቀሳቀሰ ስልጠና የተባለውን ጨርሶ እንደተፈታ ያወሳል። በተለያዩ የማጎሪያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ምርመራ የተካሄደባቸው በርካታ ሲሆኑ ከደረሰባቸው አሰቃቂ የሆኑ የማሰቃያ ድርጊቶች መካከል የሚከተሉትን ይገለጻሉ። ብልት ላይ ውሃ የሞላ ፕላስቲክ ማንጠልጠል፤ እጅና እግርን አስሮ ሁለት ጆሮዎችን በአንድ ላይ በድንገት መምታትና ማደንቆር፤ በእጅና በእግር ጣቶች መካከል ቀጭን ብረቶችን አስገብቶ ማሰቃየት፤ በድብደባ አካልን ማጉደል ጥቂቶቹ ሲሆኑ ከቤተ ሰብ ጋር ግንኙነት መከልከል፤ ስድብና ዛቻ፤ በአንድ ክፍል ውስጥ ከ100 በላይ ሰዎችን ማጨቅ፤ አስገድዶ የጉልበት ስራ ማሰራት፤ በቂ ምግብ አለማቅረብ፤ የህክምና እጦት፤ ንጽህና መጠበቂያ አለመኖር (በተለይ ለሴቶች) ሜዳ ላይ በጋራ በአንድ ላይ እንዲጸዳዱ ማድረግ፤ የዘወትርና የተለመዱ የማሰቃያ መንገዶች መሆኑን የተፈቱት ዜጎች ይገልጻሉ። በማሰቃየት ተግባር ላይ የተሰማሩትም በአብዛኛው የወያኔ አባላት መሆናቸው ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials