Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, January 17, 2017

ኢትየጵያ ውስጥ ብሔር የሚባል ነገር የለም- ከ ኤርሚያስ ቶኩማ

ኢትየጵያ ውስጥ ብሔር የሚባል ነገር የለም


አንዳንዴ ረገጥ አድርጎ መፃፍ ትክክል ነው ከላይ ከላይ ስንደባብሰው እውነታው ሳይነገር ያልፋል፡፡ ለዚህም ነው ይህንን ፅሁፍ መድገም ያስፈለገኝ መንግስት ብሔርህ ይሄ ነው ስላለን ብቻ ሳናቅማማ ተቅብለን የምሞትለት ብሔር ይሄ ነው ማለት ያሳፍራል፡፡ እኔ የምሞትለት ወይም የምኖርለት ብሄር ኢትዮጵያ ብቻ ነው ምክንያቱም ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ብሔር አለ የለም የሚለውን ከመመለሳችን በፊት የብሔርን ምንነት በቅጡ ልንረዳው ይገባል፡፡ 
ብሔር የግዕዝ ቃል ነው ይህ ቃል “Nation” ከሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ጋር ብቻ ነው አቻ ትርጉም የሚኖረው በአማርኛ “ሀገር” እንደማለት ነው፡፡ ብሔር አንድ ሀገር ህዝቦች መጠሪያ እንጂ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ጎሳዎች መጠሪያ ሆኖ አያውቅም፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ብሔር፣ የኬንያ ብሄር ወይም የጀርመን ብሔር አለ ምክንያቱም እነዚህ ሶስት ሀገራት ብሔር (ሀገር) (Nation) ናቸው፡፡ በአንፃሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ኦሮሞ፣ አማራ፣ አፋር፣ ሀዲያ፣ ጉራጌ፣ ሶማሊ፣ ትግሬ፣ ጋምቤላ፣ ሀደሬና ሌሎችም በአንድ ሀገር ውስጥ ከሌሎች ጎሳዎች ጋር እየኖሩ ብቻቸውን ጎሳ መሆን አይችሉም፡፡
ከላይ ከጠቀስኳቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ጎሳዎች መካከል የአፋር ጎሳን ወስደን ብሔር ሊያሰኘው የማይችልባቸውን ምክንያቶች እንመልከት፡፡
የአፋር ጎሳ የራሱ ብሄር ሊያሰኘው የሚችለው የራሱ የሆኑ ቀላሎቹ ብሔራዊ የመገበያያ ገንዘብ እና ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊት እንኳን የለውም ሆኖም ገዢው ፓርቲ አፋር አንድ የተለየ ሀገር (ብሔር)(Nation) ነው ለማለት ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር አዘጋጅቶለታል፡፡ በነገራችን ላይ ጎሳዎች የየራሳቸው ባንዲራ ያላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው በሌሎች ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ጎሳዎች በስቴት ደረጃ የተደራጁ የፌድራሊዝም ስርዓት ተከታይ የሆኑ ሀገራት ውስጥ ቢሆኑ እንኳን የመጡበት ስቴት አርማን ነው እንጂ የሚጠቀሙት ለብቻቸው የራሳቸው ሰንደቅ ዓላማ አይኖራቸውም፡፡
ይህ የኢትዮጵያ ህዝብን በጎሳ ነጣጥሎ እንደብሄር መመልከት የተጀመረው ከጆሴፍ ስታሊን Perestroika መርህ በመነሳት ነው፡፡ በጆሴፍ ስታሊን በፔሬስትሮይካ መርህ መሰረት የሶቭየት ህብረትን ለመመስረት አዘርባጃን፣ ካዛኪስታን፣ ጆርጂያ፣ላቲቪያ፣ ሉቲንያ፣ ታጂኪስታን፣ ተርኪሜንስታን፣ ዩክሬይን እና ኡዝቤኪስታንን በማካተት የራሺያን ፌዴሬሽን ተመሰረተ እናም ከተለያዩ ሀገራት (ብሄሮች)(Nation) የተመሰረተ የራሺያ ፌዴሬሽን ስለነበረ በፌዴሬሽኑ ስር ላሉት ሀገራት በሙሉ ልክ ዛሬ ገዢው ፓርቲ ብሔር ብሎ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደከፋፈለው የካዛኪስታን ብሄር፣ የላቲቪያ ብሔር፣ የዩክሬይን ብሄር እያለ እንዲጠሩ አደረገ፡፡ ስታሊን ትክክል ነበረ ምክንያቱም ሀገራቶቹ በፌዴሬሽን ይተሳሰሩ እንጂ የተለያዩ ሀገራት አይድሉም በአንፃሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ኦሮሞ፣ አማራ፣ አፋር፣ ሀዲያ፣ ጉራጌ፣ ሶማሊ፣ ትግሬ፣ ጋምቤላ፣ ሀደሬና ሌሎችም የተለያዩ ጎሳዎች እንጂ የተለያዩ ሀገራት አይደሉም፡፡ ህዋሃት ለኢትዮጵያ ታሪክ ካለው ጥላቻ የተነሳና ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቸው በማሰብ የብሔር ፖለቲካን በተሳሳተ መንገድ አስረድቶ ብዙ ፍታ መግባትን ፈጥሯል። በነገራችን ላይ የሕወኃት አመራሮች መሃይም በመሆናቸው ነው የብሔር ፖለቲካ አቀንቃኝ የሆኑት እንጂ የአንድነት አቀንቃኞች መሆን ቢችሉ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆን ይችሉ ነበረ፤ ምክንያቱም ምንም ጊዜ ከአነስተኛ ቁጥር ካላቸው ጎሳዎች ወጥተህ ሀገር መምራት ስትጀምር ሕዝቡን እርስ በእርስ እያጣለሁ ሥልጣን ላይ መቆየት እችላለሁ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው ምክንያቱም ሰው ጎሰኛ በሆነ መጠን አነስተኛ ጎሣ ካላቸው ውስጥ የሚመጣ መሪን ሊቀበል የሚችልበት ምክንያት አይኖረውም በአንፃሩ አንድነቱ የጠነከረ ህዝብ ከፈጠርክ ከትንሽ ጎሳ ና ከትልቅ ያንተ ጎሣ ምንነት ለሕዝቡ ጥያቄ አይሆንም። ጥንታዊ የኛ ቀደምት አያቶች በማዕከላዊ መንግስት ስር በአንድ ላይ ባያስተዳድሩንም ለየብቻችን ሀገር የነበርንበት አንድም የታሪክ ማስረጃ የለም ታድያ እንዴት ለየብቻችን ሀገር (ብሔር)(Nation) መሆን እንችላለን፡፡
ለዛም ነው ዘወትር ኢትዮጵያዊነት በዘርና በቋንቋ የሚለካ አይደለም፡፡ ሰዎች የመጣባቸውን ችግር ለመቋቋም ባደረጉት ትግል፣ ባገኙት ውጤትና ስኬት ውስጥ ያለፈ ፍልስፍና ነው የሚለውን የፕሮፌሰር ማሞ ሙጬን አባባል የምለጥፈው፡፡ ኢትዮጵያዊነት የጎሳ ትርጉም ያለው አይደለም ቋንቋ የሰውን ልጅ ሊከፋፍል አይገባውም የምለው፡፡ ለዛም ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ጎሳ እንጂ ብሄር የለም የምለው ጎሳችን አፋር፣ ጉራጌ አልያም ሺናሻ ልንሆን እንችላለን ብሄራችን ግን ኢትዮጵያዊነት ነው የምለው::
#ኤርሚያስ_ቶኩማ

No comments:

Post a Comment

wanted officials