Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 18, 2017

በጎንደር አዘዞ የወያኔ ቃል አቀባይና ሕዝብን እየጠቆመ እንዲሰቃዩ ሲያስደርግ የነበረው ነጋ እርቅይሁን በመኪና ተገጭቶ እንዲሞት ተደረገ



(ዘ-ሐበሻ) በአማራ ክልል የአማራው ተጋድሎ የህቡዕ አስተባባሪዎች ከትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ጋር ለሆዳቸው አድረው በአማራው ላይ የማቃጠር ተግባር በሚፈጽሙትና ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አልያም እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ባስጠነቀቀው መሠረት አላርፍ ባሉት ላይ እርምጃ መውሰዱን ቀጥሏል::
በጎንደር አዘዞ ከተማ የወያኔ መንግስት ዋና ቃል አቀባይና ነዋሪዎችን በማሳሰር፣ የሥም ዝርዝርና ማንነታቸውን በመግለጽ እንዲሁም ወጣቶችን ቤት ለቤት እየተከታተለ ሲያሳስር የነበረው አቶ ነጋ እርቅ ይሁን በመኪና ተገጭቶ እንዲሞት መደረጉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::
እንደምንጮቹ ገለጻ በአዘዞ ከተማ በወያኔ መንግስት ለተገደሉ ወጣቶች እና ለታሰሩት ወገኖች ዋነኛው ተጠያቂ ግለሰብ ነው የተባለው አቶ ነጋ እርቅይሁን ላይ እንዲህ ያለው እርምጃ የተወሰደበት በተደጋጋሚ ሲመከር አልሰማ በማለቱና በማን አለብኝነት የአካባቢውን ሕዝብ በመጠቆም እንዲሰቃይና እንዲሞት በማስደረጉ የአዘዞ ሕዝብ በመማረሩ ነው::
ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ ላይ በተመሳሳይ ደረጀ መከታው የተሰኘው ከወያኔ ደህንነት ጋር በመሆን በአሳቻ ሰዓትና በማታ ንፁሃን ዜጎችን በማደን ሲያሳስርና ሲያስደበድብ በተጨማሪም ሲያስገድል የቆየ የተባለ ግለሰብ እርምጃ ተወስዶበት ሕይወቱ ማለፉን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::
የአማራ ተጋድሎ የህቡዕ አስተባባሪዎች “አሁንም ሕዝብ ላይ እየጠቆሙ እንዲሰቃዩ እያስደረጉ ያሉ አላርፍ ባሉ ባንዳዎች ላይ የምንወስደውን እርምጃ እንቀጥላለን” ማለታቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials