የሱዳን መንግስት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሁለት አዉቶቡሶችን ለገሰ
ባለፈዉ ሰኔ የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኡመር አልባሽር የአፍሪካን የክብር ሻምፒዮን ተብለዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኔልሰን ማንዴላ አዳራሽ ዉስጥ ተካሒዶ በነበረዉ የአፍሪካ የክብር ሻምፒዮን ፎረም ላይ በተካሔደዉ የሽልማት ሥነ ስርዓት ላይ ሽልማቱን በተቀበሉበት ጊዜ በገቡት ቃል መሰረት እንደሆነ ታዉቋል።
በርክክቡ ላይ አዲስ አበባ የሚገኘዉ የሱዳን አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ጀማል አል ሸኪህ አሕመድ እንደተናገሩት ስጦታዉ የሚያመላክተዉ በሁለቱ አገሮች ለረጅም ጊዜ አብሮ የኖረዉን የአብሮ መኖርና በጋራ መሥራትን የሚያመላክት ነዉ ብለዋል። አሕመድ እንዳሉት ኢትዮጵያና ሱዳን ታሪካዊ ወዳጅነት ያላቸዉ እንደመሆናቸዉ በሁለቱ አገራት ዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ ያለዉን የባሕል ልምድ ልዉዉጥ በማክበር ለወደፊትም አጥብቀዉ እንደሚሰሩበት ገልፀዋል።
የአዲስ አበባዉ ዪኒቨርስቲ ፕሬዚደንት የሆኑት ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ በርክክቡ ላይ ባደረጉት ንግግር እነዚህ አዉቶቡሶች ዩኒቨርስቲያቸዉ ያለበትን ችግር እንደሚያቀልላቸዉ በተለይ ወደ ኢንዱስትሪ እና የቢዝነስ ተቋማት ፊልድ ለመሄድ የነበረባቸዉን ችግር እንደሚያቃልል ገልጿል። እንደ ዩኒቨርስቲዉ ፕሬዚደንት ገለፃ በሁለቱ አገሮች ዩኒቨርስቲዎች እና ሌሎች ክፍተኛ ተቋማት መካከል ሊኖር ስለሚገባዉ ትብብር እየሰሩም እንደነበር ገልፀዋል።
የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኡመር ሐሰን አልባሽር እነዚህን አዉቶቡሶች ለመስጠት ቃል ገብቶ የነበረዉ የአፍሪካ የክብር ሻምፒዮን ተብለዉ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሚገኘዉ የኔልሰን ማንዴላ አዳራሽ ዉሰጥ በተካሔደዉ የሽልማት ስርዓት ላይ በተሸለሙበት ጊዜ እንደነበር ሪፖርቱ አያይዞ ገልጿል። የሱዳን ትሪቡን እያንዳንዱ አዉቶቡስ 50፣000 ዶላር ሊያወጡ እንደሚችሉም በዘገባዉ አካቷል።-
No comments:
Post a Comment