Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, January 28, 2017

በኦጋዴን የሚታየውን ረሃብ መንግስትና አለማቀፍ ድርጅቶች ሆን ብለው አሳንሰውታል ሲል ኦብነግ አስታወቀ

የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ለኢሳት በላከው መግለጫ በኦጋዴን ለሁለት ተከታታይ አመታት የተቛረጠው ዝናብ በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳትን መግደሉንና ህዝቡንም ለአደጋ እንዳጋለጠው ጠቅሷል።
አብዛኞቹ የኦጋዴን አካባቢዎች ለከፋ የውሃ እጥረት የተጋለጡ ሲሆን እንስሳትም የሚመገቡት አጥተዋል። ህዝቡ ችግሩን ለማቋቋም እንዳይችል የንግድ የእርዳታ እና የመገናኛ ብዙሃን አፈና ተጥሎበታል የሚለው መግለጫው በተለይ ልጆች በውጭ አገራት ያሉዋቸው ቤተሰቦች በሚላክላቸው ገንዘብ ምግብ እንዳይገዙ እንኳን የሚገዛ ምግብ ገበያ ላይ መጥፋቱን ያትታል።
ቀይመስቀልና ሌሎች አለማቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የእርዳታ አቅርቦት እንዳያደርጉ መከልከላቸው እንዲሁም በአካባቢው ያለውን ችግር አለም ህዝብ የሚያቀርብ ነጻ ሚዲያ መጥፋቱ ችግሩን እንዳባባሰው ድርጅቱ ገልጿል።
በአካባቢው የኮሌራ በሽታ ቢከሰትም የኢትዮጵያ መንግስት መደበቁን ከሁለት ቀናት በፊት በርካታ ሰዎች ቀብሪ ደሃር ላይ በዚህ በሽታ ተጠቅተው መሞታቸውንም አክሎ ገልጿል።
መንግስትና አለማቀፍ ድርጅቶች ረሃብ መከሰቱን ቢገልጹም የአደጋውን መጠን ግን አሳንሰውታል ሲል ግንባሩ ወቀሳ ያቀርባል። መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ እንደመጣር መሸፋፈንን እንዳማራጭ እየተጠቀመበት ነው የሚለው ኦብነግ በሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶአደሮች እያለቁ የአርብቶ አደሮችን ቀን በሚል በጅጅጋ ከፍተኛ ድግስ መዘጋጀት ምጸት ነው ብሎአል።
ኦብነግ የአለማቀፉ ማህበረሰብ በአስቸኳይ ለኦጋዴን ህዝብ እንዲደርስና መንግስትም በሩን ለአለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ክፍት እንዲያደርግ ጠይቋል።
በዚህ አመት በሶማሊ በደቡብና የኦሮምያ አንዳንድ አካባቢዎች የከፋ ድርቅ መከሰቱን አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ገልጸዋል።
በቅርቡ ድርጅቶቹ ከመንግስት ጋር በመሆን ባወጡት መግለጫ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህን ለመሸፈንም ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ይፈልጋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials