Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 8, 2017

የሰማያዊው ፓርቲ አቶ ጌታቸው አርበኞች ግንቦት 7ን ይቀላቀላል በሚል ስጋት ዋስትና ተከለከለ

የሰማያዊው ፓርቲ አቶ ጌታቸው አርበኞች ግንቦት 7ን ይቀላቀላል በሚል ስጋት ዋስትና ተከለከለ
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዋለው ችሎት የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን ዋና  አዘጋጅ በሆኑት የአቶ ጌታቸው ሽፈራው  የዋስትና መብት ጥያቄ ተመልክቷል።Image may contain: 1 person
አቃቢ ህጉ ለፍርድ ቤቱ ተከሳሹ የዋስትና መብቱ ቢጠበቅለት በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘውን የአርበኞች ግንቦት 7ን ይቀላቀላል በማለት ክሱን አስደምጧል።
አቃቢ ህጉም አክሎ አርበኞች ግንቦት አገር ውስጥ ያለውን ውስብስብ አደረጃጀት በመጠቀም በቀላሉ ተከሳሹን ከአገር ሊያስወጣው ይችላ የሚል መከራከሪያ አቅርቧል።
በርግጥም አቶ ጌታቸው ሽፈራው የዋስ መብታቸውን የሚያስከብር አንቀጽ ቢኖርም ፍርድ ቤቱ ትጥቅ ትግሉን ሊቀላቀሉ ይችላሉ በሚል ስጋት የዋስትና መብታቸውን ገፏቸዋል።
አገዛዙን በብረት ለመለወጥ ከሚንቀሳቀስ ድርጅት ጋር የስራ ቁርኝነት ፈጥሯል እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይም የሰላ ትችት በህውሃት/ኢሕአዴግ ላይ አቅርቧል በማለት አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው ላይ ክስ ከዚህ ቀደምም አቅርቦ እንደነበረ ይታወቃል።
ፍርድ ቤቱ የተከሳሹን የአቶ ጌታቸው ሽፈራውን የዋስትና መብት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ ለየካቲት 7ቀን 2009ዓም አስተላልፏል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials