Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, January 3, 2017

ለአንባብያን በተለይ ለፕሮፌሰር ጌታቸው የተላከ የመሪራሰ አማን በላይ መልእክት እነሆ










Image may contain: 1 person
ለአንባብያን የተላከ የመሪራሰ አማን በላይ መልእክት እነሆ--- ይድረስ ይህን ለምታነቡ ሁሉ የሃገሬ ሰዎች፣

 የተወለድኩት፣ የአደግኩትና የተማርኩት በዛው በጎንደርና በጎጃም ነው፡፡ የትውልዴ ስፍራ በለሳ ነው፡፡ አባቴ መምህር በላይ ድሉ ካህን ነበሩ፡፡ ከውድ አባቴ ከ መምሀር በላይ፣ከአባ ጼሄማ በጎንድ ተክለሃይማኖት፣ ከመሪጌታ መንክር ደብረኤልያስ ጎጃም፣ ከመሪጌታ ጉባኤ በዛው በጎጃም፣ ቅዳሴን፣ ቅኔን፣ ዜማን፣ ብሉይን፣ ሃዲስን፣ የእንጨት አዋጅን (የመድሃኒት እጽዋትን)፣ የሃረግ ስእልን፣ የኢትዮጵን ታሪክ፣ አቡሻህርን (ባህረሃሳብን)እና ሌሎችንም በአድባራት እና ገዳማት የሚሰጡ የኢትዮጵያን ትምሀርቶችን በሚገባ ተምሬአለሁ;; በለተይ በቅኔ፣ በግስ ርባታ እና ሰዋስው ችሎታዬ በመምህራኔ እና የትምሀርት ባልንጀሮቼ ስሜ የተጠራ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት በጎጃም በይስማ ደጀን በመሪጌታ መንክር ዘንድ ቅኔ አስነጋሪ ነበርኩ፡፡ ተማሪ ሳለሁና ትምሀርቴንም ካጠናቀቅኩ በሁዋላ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተዘዋወርኩ አያሌ ገዳማትን እና አድባራትን እየጎበኘሁ በውስጣቸው የአሉትን ምሰጢራዊና ጥንታዊ መጻህፍቶቻችንን ለመመርመር እድል አግኝቻለሁ;;

የ 18 ዐመት ልጅ ሁኜ ወደ ኑበያ (ሱዳን) ተጉዤ በነበረበት ወቅት በአንድ በፈራረሰ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቤተክተርሰትያን ቅጥር ግቢ በተቀበረ የድንጋይ ሳጥን ውስጥ ምናልባት ኢትዮጵያ ውስጥ የሌሉ የኢትዮጵያን ታሪክ ጨምሮ ስለተለያዩ ጉዳይዎች የሚዘረዝሩ በግእዝ የተጻፉ የብራና መጻህፍትና ጥቅሎች አገኘሁ፡፡ 

ስለ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ አስተዋፅኦ 

ለፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ የተሰጠ መልስ (ክፍል አንድ) 








ውድ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ለጤናዎ ባያሌው እንደምን ሰነበቱ? ድምፆቻችንን ከተሰማማን ብዙ ጊዜ ሆነን ኣይደል? እኔ ለጤናዬ እግዚአብሄር ይመስገን ደህና ነኝ፡፡ ርስዎን እንደ አላመምዎት ተስፋ አደርጋለሁ;; የእኔን አዲስ መጽሃፍ አስመልክቶ ርሰዎ ስለተቹት ከመመለሴ በፊት፣ የተከበሩት ሊቀ-ሊቃውንት መሪራሰ አማን በላይ ለአንባብያን አስተላልፍላቸው ዘንድ የሰደዱልኝን የአደራ መልእክት አቀርባለሁ፡፡ ከዛ በሁዋላ ወደ ራሴ ምላሽ እሸጋገራለሁ፡፡





 ለአንባብያን የተላከ የመሪራሰ አማን በላይ መልእክት እነሆ--- ይድረስ ይህን ለምታነቡ ሁሉ የሃገሬ ሰዎች፣























ይህ የሆነው የዛሬ 50 ዐመት አካባቢ ነበር;፡፡ እነዛን መጻህፍት ይዤ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ ከነሱ ውስጥ አውጣጥቼ አሳጥሬና መጥኜ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ታሪክ በሚል ርእስ እንድ መጽሃፍ ጽፌ ለማሳተም ሞክሬ ነበር፡፡ ሆኖም ዶክተር ኃይሉ ወልደአብ የሚባሉ ሀቀኛ ሙሁር ብራናዎቹን መርምረው፣ ይህ አንተ የጻፍከው መጽሃፍ እውነተኛው ታሪካችን በመሆኑ እሰከዛሬ የተጻፉትን ስለሚቃረን ችግር ይደርስብሃል፤ ስለዚህ አቆየው፣ ብለው መከሩኝ፡፡ እኔም ቀና ምከራቸውን ሰምቼ የደርግንም የሽብር ዘመን አሳልፌ፣ መጽሃፉን በሚስጥር አቆይቼው ኖሬ የዛሬ 24 ዐመት አካባቢ በድፍረት አሳተምኩት፡፡ ከዛ በሁዋላ በብርቅዬዎቹ ብራናዎች ላይ ተመርኩዤ አያሌ መጻህፍትን እያከታተልኩ አወጣሁ፡፡ በወቅቱ በደረሰኝ መረጃ መሰረት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ የእኔን መጻህፍት ከማንበብ አልፈው ከነሱ ውስጥ እየጠቀሱ በአደባባይ ተጠቅመውባቸውል፡፡ ዘግይተውም ብራናዎቹን እጃቸው ለመክተት የሁለታችንም ወዳጅ የሆነውን ላይብረሪ ኦፍ ኮንግረስ የሚሠራውን አቶ ፈንታሁን ጥሩነህን እና ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን አማላጅ ልከው እባክህ ብራናዎቹን ልመርምራቸው፣ አሉኝ፡፡ 2 እኔ ግን ከዚህ በፊት ሌሎች ምሁራን ነን የሚሉ ሰዎች እንደዚሁ ብራናዎቹን አሳየን ብለውኝ ባሳያቸው ሊወስዱብኝ ሞክረው ስለነበር ከስህተቴ ተምሬ ብራናዎቹን ለፕሮፌስር ጌታቸው ኃይሌ ለመስጠት አልፈቀድኩም፡፡ ደግሞም ንብረቶቹ የኔ የግሌ ስለሆኑ የራሱን ንብረት ለደቂቃስ ቢሆን ያለዋስትና ማን ለማን ይሰጣል? ከዚህም በተጨማሪ ታሪከ-ነክ እና ባህረሃሳብን ጨምሮ ፕሮፌሰሩ የጻፉአቸውን መጻህፍት ሳነብ ምንም የታሪከ አውቅት የሌላቸውና የግእዝ ችሎታቸውም ደረጃ በጣም ዝቅ ያለ ሆኖ ስለአገኘሁት፣ በባህረሃሳባቸውም ውስጥ ከባድ ስህተት ፈጽመው ስለዐየሁአቸው የእኔን የግእዝ ብራናዎች፣ ያውም በጥንታዊ ግአዝ የተከተቡትን ተረድተው ለመፍረድ በጣም እንደሚያስቸግራቸው ተከሰተልኝ፡፡

 ከዚህም በላይ፣ እኚህ ግለሰብ ሊቃውንት አባቶቻችንን ኢትዮጵያውያንን ስለሚንቁና አረቦችን፣ ግሪኮችንና አውሮጵያውያንን እያወደሱ ‹‹አባቶቻችን‹‹ ስለሚሉ ለኢትዮጵያውያን የአላቸው ፍቅር እና ከበሬታ አጠራጣሪ ሆነብኝ፡፡ በመጨረሻም፣ ሰውየውን ስለማላምናቸው በቀላሉ የማይገኝ ንብረቴን ከእጄ ማውጣት ጨነቀኝ፡፡ የማላምናቸውም፣ የገቡበትን ሁሉ ድርጅት አፍርሰው የሚወጡ ናቸው፣ ሲሉ ስለሰማሁና የኑሮ መተዳደሪያቸውም ፈረንጆች በርካሽ ገዝተውም ሆነ ሰርቀው ያከማቹአቸውን የኢትዮጵያ ብራናዎችንና ቅርሶችን መመዝገብና ማቀናጅት ነው ስለተባለ ነው፡፡ ይህ በመባሉም እኔ ያገኘሁአቸውን ለትውልድ ላስተላልፍ ያቀድኩአቸውን ብርቅዬ ጥንታዊ ብራናዎች ለእኚህ ሰው ይመርምሩ ብዬ ሰጥቻቸው የደለበ ደሞዝ ለሚከፍሉአቸው ፈረንጆች እሳቸው ቢዳርጉአቸውና እነዛ ፈረንጆች በውድ ዋጋ ቢሸጡአቸው ወይም ብራናዎቹ በሚመሰክሩት የኢተዮጵያ ታላቅነት ፈረንጆቹ ቀንተው ቢያጠፉት አለዛም ለኢትዮጵያ ጠላቶች አሳልፈው ቢሰጡአቸው የማን ያለህ ልል ነው፣ በሚል ስጋት ስለተጨነኩም ነበር;; እንግዲህ እላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ብራናዎቹን ስለከለከልኩአቸው ፕሮፌሰሩ ተናደው አማን በላይ ምንም ብራናዎች የለውም፤ ይህን ሁሉ መጽሃፍ የሚጽፈው ከልቡ እያፈለቀ ነው፣ እውነት ለማስመሰልም ከኢትዮጵያ ታሪክ ያጣቅሳል፤ ብለው በሃስትና በድፍረት ውሸታምና አጭበርባሪ አድርገውኝ ስሜን አጥፍተዋል;; እሳቸው በኔ ላይ ላደረሱብኝ የስም ማጥፋት እግዚአብሄር ይበቀልልኛል፡፡ ካህኑ የእግዚአበሄር አገልጋይ አባቴ መምህር በላይም ሆነ በየደብሮቹና ገዳማቱ የነበሩት ቅዱሳን መምሀሮቼ ከቶውንም ውሸት እንዳልናገርና ለእውነት ብቻ እንድቆም በግበረገብነት እያነጹ አሳድገውኛል፡፡ ስለዚህ ልብወለድ ጽፌ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው ብዬ አላቀርብም፡፡ የጻፍአኩቸው ሁሉ መጻህፍት እውነተኛ የኢትዮጵያ ታሪክ ናቸው፡፡ በእኔ ዘንድ የሚገኙትን ብራናዎች ግን ለደህንነታቸው አስተማማኝ ጊዜ ሲደርስ የኢትዮጵያና የዐለም ጋዜጠኞች፣ እንዲሁም ሀቀኛ የሃገራችንና ዐለምአቀፍ ምሁራን በተገኙበት ሸንጎ ላይ ለባህል ሚኒሰቴር፣ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወይም ለቤተመጻህፍት ወ መዘክር አስረክባለሁ፡፡ ታዲያን በዛን ጊዜ ዋሾው እኔ ልሁን ፕሮፌሰር ጌታቸው ይለያል፡፡

 እግረመንገዴን ግን አንድ ነገር መግለጽ እሻለሁ;;--- ከኑብያ ካገኘሁአቸው መጻህፍት ውስጥ ታሪከ-ነገሥት ዘ ኢትዮጵያን ለ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኬኔዲ ቤተመጻህፍት እና የሱባንና የግዕዝ መዝገበቃላትን ለ ቤተመጻህፍት ወ መዘክር አንዳንድ ቅጂዎች አበርክቻለሁ፡፡ ዳሩ ግን ይህን ቁምነገር ብዬ በአዋጅ አላስነገርኩም፡፡ የብራናዎቹን ቅጂዎች በመስጠቴ ቤተመጻህፍት ወ መዘክር መቀበሉን የሚያንጸባርቅ የምስክር ወረቀት ሲሰጠኝ የኬነዲ ቤተመጻሀፍት ግን አመሰግናለሁ እንኩዋን አላለኝም፡፡ የ እኔ ሳያንስ፣ፕሮፌሰር ጌታቸው ውሸታም የአደረጉትና በአደባባይ የዘለፉት ሃገሩን ኢትዮጵያን የሚወደውን፣ በጎሰኝነት ጎራ ፍጹም ተሰልፎ የማያውቀውን፣ በሰብእናው ልእልና እና በምሁርነቱ ርቅቀት እጅግ የማከብረውን ወዳጄን ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን ጭምር ነው፡፡ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳም ልብወለድ ወይም (ሚት) አልጻፈም;; ከኔ መጻህፍት በተጨማሪ በ 42 በተለያዩ የታሪክ ዋቢ መጻሃፍት ላይ ተንተርሶ ነው፡፡ ከዚህ በፊት አኔም ሆንኩ ሌሎች ባለታሪኮች ያልደረሱትንና ያልደረሱበትን የሀገራችንን አደገኛ ውጥረት የሚያረግብ መጽሀፍ የጻፈው፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ የተሰኘው መጽሃፉ የርሱ የራሱ፣ ላቡን አንጠፍጥፎ፣ እውቀቱን 3 ጨምቆ፣ የጻፈው የታሪክ መጽሃፉ ነው፡፡ ይህም እጅግ የሚያስመሰግነው ድንቅ ሥራው ከዚህ ቀደም ያልነበረ ወሪጅናል እንደሆነ በዚህ አጋጣሚ ላረጋግጥ እወዳለሁ፡፡

በመጨረሻ ለፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ አማን በላይ ምንም ከሱዳን የተገኘ መጽሃፍ የለውም፣ ከልቦናው አንቅቶ ነው የሚጽፈው፤ ስለአልከው፣ ከዚህ ቀደም ለፕሮፌሰር ፍቅሬ በፍላሽ ድራየቭ ሰጥቼው ከነበረው ኑብያ ውሰጥ ካገኘሁት ጥንታዊ የብራና መጽሃፍ ላይ ጥቂት ገጾች ለናሙና እንዲያሳይ ስለፈቀድኩለት ከኮምፒተሩ ላይ ያለችግር ከታተመለት ለአንባብያን ያቀርበዋል፡፡ በኑብያ ካገኘሁአቸው መጻህፍት መሃል በቅርብ የተገኘው ይህ ብቻ ስለሆነ ነው ለጊዜው ይሀን ለህዝብ አቅርብ ያልኩት፡፡ ሌላው ጊዜና ቦታው ሲፈቅድ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቀርባል;; ፕሮፌሰር ጌታቸው አዳምጥ፣--- እኔና የግዕዝ ሊቃውንት በተለያዩ ጊዜያት የግዕዝ ችሎታህን እንደገመገምነው በጣም ደካማ ነው፡፡ ከልምምድ ብዛት ያካበትከው እንጂ በቅጡ የተማርከው አይደለም፡፡ ግዕዝ ለማያውቁ ሰዎች ግዕዝ የምትችል መስለህ ትታያቸው ይሆናል፡፡ ባህረሀሳብ ባልከው መጽሀፍ ውሰጥ እንኩዋን ግዙፍ ግዕዛዊና ቀመራዊ ስህተቶች ሠርተሃል፡፡ የአንተን ባህረሀሳብ ምንነት፣ ምንጭና ስህትት አስመልከቶ የጻፍኩት ራሱን የቻለ መጽሀፍ ስለማወጣ ነቀተህ ተጠባበቅ፡፡ አሁን ለጊዜው ግን፣ በርካታ ብራናውን ተወውና እስቲ እነዚህን ፕሮፌስር ፍቅሬ ለናሙና ያቀረባቸውን የግእዝ ገጾች ወደ አማርኛ ተርጉመህ ችሎታህን አሳየን፡፡ ከዛ በሁዋላ ስለ ሌሎቹ መጻህፍት እንነጋገራለን፡፡ በመጨረሻም፣ መሪራሰ አማን በላይን እኔ ወደ እኔ ና ብዬው ሳይመጣ ቀረ ስለ አልከኝ ከኔ አንድ ነገር ለማግኘት የፈለግከው አንተ ስለሆንክ ወደ እኔ መምጣት የነበረብህ አንተ ነህ፡፡ አንተ ትፈልገኛለህ እንጂ ለእኔ አታስፈልገኝምና;; ለጊዜው በእዚሁ ልሰናበትህ፡፡
መሪራስ አማን በላይ፣ ጸሀፌ-ታሪክ
እኤአ ታህሳስ 21 ቀን 2016

ውድ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ ከዚህ በታች የሰፈረው ደሞ እኔ ፍቅሬ ቶሎሳ ለ እርስዎ የጻፍኩት ነው;;

No comments:

Post a Comment

wanted officials