Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, August 1, 2015

አቶ አብርሃም ጌጡ በቤተሰብና በጠበቃ እንዳይጠየቅ ተከለከለ

አቶ አብርሃም ጌጡ በቤተሰብና በጠበቃ እንዳይጠየቅ ተከለከለ
ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia
በአቶ ማሙሸት አማረ ካቢኔ የመኢአድ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበረው አቶ አብርሃም ጌጡ በቤተሰብና በጠበቃው እንዳይጠየቅ መደረጉን ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጹ፡፡ አቶ አብርሃም ጌጡ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም ቤቱ በፖሊስ ተከቦ ከታሰረ በኋላ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ጉዳዩን በልደታ ፍርድ ቤት ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ ተደጋጋሚ ቀጠሮ ከሰጠው በኋላ ምርመራዬን አልጨረስኩም ላለው ፖሊስ ‹‹የመጨረሻ ቀጠሮ›› በሰጠበት ወቅት ፖሊስ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በማዛወር አራዳ ፍርድ ቤት ሲያቀርበው እንደቆየ ተገልጾአል፡፡
አቶ አብርሃም ጌጡ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰበት የገለጹት ቤተሰቦቹ ሀምሌ 12/2007 ዓ.ም ወደ ማዕከላዊ ምርመራ መዛወሩን ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ወደ ማዕከላዊ ከተዛወረ በኋላ በቤተሰብና በጠበቃውም እንዳይጠየቅ በመከልከሉ ያለበትን ሁኔታም ለማወቅ መቸገራቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ወደ ማዕከላዊ እንደተዛወረ ብናውቅም በአሁኑ ወቅት የት እንዳደረሱት እርግጠኛ መሆን አልቻልንም›› ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials