Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 3, 2015

በአብድራፊና በሶረቃ ከተማ የህዝብ ተመራጮች እየተያዙ ነው

በአብድራፊና በሶረቃ ከተማ የህዝብ ተመራጮች እየተያዙ ነው

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ ህዝቡን አስተባብረዋል የተባሉ ሰዎች እየታሰሩ ሲሆን፣ ሌሎች አመራሮችም እየታደኑ ነው።
የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአካባቢው ለተፈጠረው ውጥረት ተጠያቂ ናቸው ተብለው ከተጠረጠሩት መካከል አቶ አዋጁ አቦሃይ ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2007 ዓም በ8 የፌደራል ፖሊሶች መሳሪያቸውን ተቀምተው ታስረዋል። ሶረቃ ውስጥ የሚኖሩ አቶ ደጀን የተባሉ ሰውም በፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ የደረሱበት አልታወቀም። የፌደራል ፖሊስ አባላት ሃይሌ ማሞ የተባለውን የአካባቢው ተወላጅ ለመያዝ እንቅስቃሴ የጀመሩ ቢሆንም፣ ግለሰቡ ግን ከአካባቢው መሰወሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አካባቢው በልዩ ሃይል እየተጠበቀ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ህዝቡ ለ23 አመታት የተጫነው ቀንበር ይበቃናል በማለት ተቃውሞ እያሰማ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በርካታ የሰሜን አርማጭሆ ተወላጆች መንግስትን በሃይል ለማውረድ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሃይሎች ጋር እየተቀላቀሉ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials