Source : Abakostir Belay
ሰበር ዜና !!
ድርጊቱን ባልደግፈዉም ትኩስ ገራሚ መረጃ እነሆ:-
"ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በተወረወረ ጫማ ተመቱ!"
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ትላንት ፣ የካቲት 18 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቤተ መቅደስ ከምእመናን አቅጣጫ በተወረወረ ቀይ ሸራ ጫማ መመታታቸው ታወቀ ፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩን ጫማ በመወርወር የመታው ግለሰብ አስቻለው ግቢ አናጋው ሲባል ፤ የወረወራቸው የኹለት እግሩ ጫማዎች አንዱ ቅዱስነታቸውን ሲመታ ሌላው የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ የኾኑትን ንቡረ እድ አባተ ጠምቀን መምታቱን በሥፍራው የነበረው ምንጫችን መመልከት ችሏል ፡፡
እንደምንጫችን ዘገባ ከኾነ ቅዱስ ፓትርያርኩን ጫማውን በመርወር የመታው አስቻለው ጫማውን እየወረወረ ‹‹ ሌባ ፤ የሌባ ወዳጅ ፤›› ሲል ተደምጧል ፡፡ ቅዱስነታቸውም በድንጋጤ ሲያማትቡ ታይተዋል ፡፡
አስቻለው ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ለማምለጥ ሲሞክር ፓትርያርኩን በማስመረጥ ዋነኛ ተዋናይ የነበሩት የአሲራ መቲራ ገዳም አስተዳዳሪ የኾኑት አባ ገብረ መድኅን እና መምህር ወንድ ይፍራው ተስፋይ ተረባርበው ይዘው በመደብደብ ለፖሊስ ሲያስረክቡ ማየታቸውን የዐይን እማኞች ገልጠው ፤ የመጡትም ፖሊሶች እየደበደቡት ወደ ኹለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሲወሰወዱት ማየታቸውን ለምንጫችን አረጋግጠዋል ፡፡ ንቡረ እድ አባ ተጠምቀ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ ፣ መምህር ሙሴ ኀይሉ የፓትርያርኩ ፕሮቶኮል ፣ አባ ኪሮስ የፓትርያርኩ የካሜራ ባለሙያ ለፖሊስ ምስክር ኾነው መቅረባቸውን ለማወቅ ተችሏል ፡፡
No comments:
Post a Comment