Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 17, 2015

የዓለም ባንክ የዓለማችን ደሀእና ባለጸጋ ሀገሮችን የሚያሳይ ጥናት ይፋአደረገ ።



የዓለም ባንክ የዓለማችን ደሀእና ባለጸጋ ሀገሮችን የሚያሳይ ጥናት ይፋአደረገ ።

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በዓለም ባንክ አዲስ መረጃ መሰረት ፤ ከአስሩ የዓለማችን የመጨረሻ ሀገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች ።
በጥናቱ በድህነት ከ 1 እስከ 10 የተመዘገቡት እንደ ቅደም ተከተላቸው ማላዊ ፣ ቡሩንዲ ፣ቻድ ፣ ኒጀር ፣ ላይቤሪያ ፣ ማዳካስካር ፣ ኮንጎ ፣ጋምቢያ ፣ኢትዮጵያና ጊኒ ናቸው።
እንደተለመደው ሁሉ በዘንድሮውም ጥናት በድህነት ተርታ የተመደቡት አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ሲሆኑ ፤ ከነኚህ መካከል በመጨረሻዎቹ የድህነት ጠርዝ ላይ የተቀመጡት ከሳህራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።
የትምህርት ፣የጤናና ሌሎችንም ማህበራዊ አገልግሎቶች በማካተትና ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢን መሰረት በማድረግ ይፋ በሆነው የዓለም ባንክ ጥናት አውሮፓዊቷ ሉክሰምበርግ የመጀመሪያዋ ባለጸጋ ሀገርተ ብላለች።
እንደጥናቱ የአንድ ሉክሰምበርጋዊ ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከ110 ሺህ ዶላር በላይ ደርሷል።
ኖርዌይ፣ ኳታር፣ የቻይናዋ-ማካኦሳር፣ ስዊዘርላንድ፣ አውስትራሊያ፣ ስዊድን ፣ዴንማርክ ፣ሲንጋፖርእና አሜሪካ እንደ ቅደምተከተላቸው ከ 2 እስከ 10 ያለውን ቦታይዘዋል።
የአንድን ሀገር አጠቃላይ ገቢ ለሀገሬው የህዝብ ብዛት በማካፈል የሚገኘው ይህ ግርድፍ ስሌት ፤የአንድን ሀገር ጠቅላላ ሀብት ቢያሳይም ፣የነዋሪውን የድህነትና የሀብት ሁኔታ ምስል በትክክል እንደማያመለክት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials