Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, February 9, 2015

ከምባታ ህዝብ ነገ የተቃውሞ ሰልፍ ሊወጣ ነው

ከምባታ ህዝብ ነገ የተቃውሞ ሰልፍ ሊወጣ ነው
የከምባታ ህዝብ ሆን ተብሎ መሰረተ ልማት እንዳይገነባለት በመደረጉና በተራድኦ ድርጅቶች የተሰሩት መሰረተ ልማቶች ስራ ላይ እንዳይወሉ በደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች እየተፈፀመበት የሚገኘውን በደል በመቃወም ነገ ማክሰኞ የካቲት 2/2007 ዓ.ም በዱራሜ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ የከምባታ ህዝቦች ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የከምባታ ህዝብ በተመሳሳይ ጉዳይ ህዳር 26/2007 ዓ.ም ዱራሜ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርጎ የነበር ሲሆን የነገው ሰልፍም የክልሉ መንግስት ችግሮቹን ለመቅረፍ ዝግጁ ባለመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ከምባታ ውስጥ ሊሰራ የታሰቡና የተጀመሩ ስራዎችን የደኢህዴን ባለስልጣናት ወደተወለዱባቸው አካባቢዎች እንደሚታጠፉ የገለጹት አቶ ኤርጫፎ አንገጫ የተባለ ቦታ ላይ ተራድኦ ድርጅት የሰራው ሪፈራል ሆስፒታል ተሰርቶ ካለቀ በኋላ መገዘጋቱን እንዲሁም ቃጫ ቤሮ ወረዳ በተራድኦ የተሰራ ሆስፒታል ስራ ላይ እንዳይውል መደረጉን በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም የሚሰሩ መንገዶች የባለስልጣናቱ ዘመዶች በኮንትራክተርነት ስለሚይዟቸው ይጠናቀቃሉ በተባሉበት ጊዜ እንደማይጠናቀቁና ለሙስና የተጋለጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በሙስና እና በዝምድና ምክንያት መንገዶች እንዳይሰሩ የሚያደርጉት ባለስልጣናቱ ህዝቡ ጥያቄ በሚያነሳበት ወቅት ‹‹መሰረተ ልማት ስለሌላችሁ ወደ ከምባታ መጥቶ ለማልማት አልተቻለም፡፡›› የሚል መልስ እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡
በከምባታ ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ በመምጣቱና የደኢህዴን ባለስልጣናት ችግሩን ለመቅረፍ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ህዝቡ የሚፈጸምበትን በደል ለማሰማት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በዱራሜ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርግ ተገልጾል፡፡ የተቃውሞ ሰልፉ ህዝቡ ራሱን በማስተባበር የጠራው መሆኑም ተገልጾአል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials