Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 17, 2015

ሶስቱ የ አፋር ነጻ አውጪ ድርጅቶች በ አንድነት ግንባር ፈጠሩ



በኢትዮጵያዊነቱ እና በሃገር ወዳድነቱ የሚታወቀው የአፋር ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ የነጻነት እና የመብት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ በአምባገነን መዳፍ ስር ያለው ሕዝብ ነጻ እንዲወጣ ወያኔን ለመጣል በትጥቅ ትግል ላይ የተሰማሩ አፍዴራ ጋድሌ እና አርዱፍ በመዋሃድ የጋራ ግንባር መፍጠራቸው እየተካሄደ ላለው ትግል አንድ እርምጃ መራመድ ትልቅ አስታውጾ ያለው ተግባር ነው::
Image result for afar national liberation movement

ፓርቲዎች ባለፉት ዘመናት በተናጠል በመታገል ምንም ውጤት እንዳላገኙ በገሃድ የታየ ጉዳይ ነው::እንዲሁም በሀገር ቤት ያሉ ድርጅቶች ሊዋሃዱ አሊያም ግንባር ሊፈጥሩ በሚፈልጉበት ወቅት የወያኔ አምባገነን ገዢ ደህንነቶቹን አሰማርቶ ከፍተኛ ወከባ በመፍተር ሰርጎ ገቦችን በማስረግ ክፍተኛ መንግስታዊ ሽብርተኝነት እና እንቅፋት እየፈጠረ ይገኛል::በቅርቡ በአስመራ የተካሄደ ውህደት እና አሁንም በአፋር ድርጅቶች መካከል የተደረገው የግንባር ምስረታ ለትግሉ ታላቅ ግብ እና እመርታ ነው::

የግንባሩን መፈጠር ተከትሎ የአርዱፍ ሊቀመንበር አቶ ኢብራሂም ሙሳ ለኢሳት እንደገለጹት ሶስቱም የአፋር ድርጅቶች በተናጠል ሆነው መዋጋታቸው ለስርአቱ እድሜ መርዘም አስተዋጽኦ በማድረጉ በቅድሚያ ድርጅቶቹ የጋራ ግንባር ፈጥረው በጋራ ለመዋጋት አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ በመድረሳቸው፣ በአንድ ወታደራዊ እዝ ስር ሆነው ለመታገል ወስነዋል።አዲሱ ግንባር ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ለመታገል ፍላጎት እንዳለውም አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials