Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, February 27, 2015

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ISIS በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት የተቀመጠው ህወሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡







ኢትዮጵያዊያኑ የእስልምና እምነት ተከታዬች ፍጹም ጨዋዎች መሆናቸውን ለመመልከት ላለፉት ሶስት ዓመታት በአገሪቱ ያደረጓቸውን ሰላማዊ ተቃውሞዎች መታዘብ ይበቃል፡፡ሺህዎች በታደሙባቸው ተቃውሞዎች አማንያኑ የሚጤስ ጧፍን ሳያጠፉ ቅጥቅጥ ሸንበቆ ሳይሰብሩ ወደየቤታቸው ተመልሰዋል፡፡
እነዚሁ ሙስሊሞች ፓርቲዎች በጠሯቸው ሰላማዊ ሰልፎች (አንድነትና ሰማያዊ) በመገኘት አቡበከር እንዲፈታ የጠየቁትን ያህል እስክንድር ነጋ፣ርዕዮት ዓለሙ፣አንዷለም አራጌና ሌሎችም ነጻነታቸውን እንዲያገኙ ጠይቀዋል፡፡
ዛሬ አርብ ከጁምዓ ሰሏት በኋላ ደግሞ ይህንኑ ድምጻቸውን ያስተጋባሉ፡፡
በአንጻሩ ስርዓቱ ISISዊ ተግባሩን በወታደሮቹ በኩል በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡እነ ጋዜጠኛ የሱፍና ሰለሞን በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ የተፈጸመባቸው ማሰቃየት ፣በኮፈሌ፣ደሴ፣በአዲስ አበባና በሌሎች ስፍራዎች አይ ኤስ አይ ኤስ (ፌደራል ፖሊስ) በወሰደው ጭፍን እርምጃ ብዙዎች ደማቸው ፈሶ ይህችን ዓለም ተለይተዋል፡፡ይህ ድርጊት መንግስታዊው ISIS የፈጸመው ከማለት ውጪ ምን ሊሰኝ ይችላል ?
ሽብርተኛው ቡድን ያርዳል፣ያሰቃያል፣ሰብዓዊ ክብርን ያዋርዳል ፡፡ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ይሀንን አጥብቀው ይቃወማሉ፡፡ነገር ግን በመንግስታዊው ሽብርተኛ ቡድን ይታሰራሉ፣ባልዋሉበት በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመሰረት አሲረናል በሉ ተብለው እንዲፈርሙ ይደረጋሉ፣ውሃ የተሞሉ ላስቲኮች ብልታቸው ላይ ተንጠልጥሎ፣እግራቸው ተገልብጦ ይገረፋሉ፣በአፍጋኒስታን፣በኢራቅ ፣በሶማሊያ ስልጠና ወስደናል እንዲሉ ይገደዳሉ፣መንግስት የለም ወይ በማለታቸው ብቻ በአደባባይ ይረገጣሉ፣በጥይት ይመታሉ፣መንግስት በሚቆጣጠረው ሚዲያ ሹማምንት ቀርበው ‹‹ሽብርተኞች ፣ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የተላኩ የጥፋት መልእክተኞች ይባላሉ፣ጥናት አቀረብን የሚሉ የሌላ ሐይማኖት መምህራን ኢትዮጵያዊያኑ ሙስሊሞች እየደረሰባቸው የሚገኘውን የመብት ጥሰት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ‹‹አክራሪዎች ››ይሏቸዋል፡፡
እውነት ብትቀጥንም ፈጽማ የማትጠፋ መሆኗ ግን የትግል ተስፋ ነው የሚለው ማን ነበር?

No comments:

Post a Comment

wanted officials