Click here to listen Pastor Takeste rape a married woman in USA
ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት “ጌታ ጠራኝ” ብሎ ወደ ፕሮቴስታንት ሀይማኖት በመሄድ ዘመናዊ የተቀማጠለ ኑሮ ላይ የሚገኘው ይህ ሰው በዛሬው የአሜሪካ ድምፅ ፕሮግራም የሰውን ሚስት አስክሮ (እሱም ሰክሮ ማለት ይቻላል) የወሲብ ሸፍጥ መፈፀሙ አደባባይ በመዋል እንጂ በድርጊት የመጀመሪያው ዘማሪ ወይም ፓስተር እንዳልሆነ ይታወቃል ። እነዚህ ወደ ዓለም ሳይሆን ከዓለም የወደቁ የሀይማኖት “መሪዎች” ነውራቸው ከሰውነታቸው አንፃር የሚገርም አይሆንም ። እነሱ “ድነናል” ብለው ከሚመፃደቁበት አንፃር ግን ጥያቄ ያስነሳል ። መዳን ልብስ መቀየር ፣ ገላን ማስባትና መኪና መቀየር ከቶም አይደለም ። ፓስተሮችና ዘማሪያን ሀይማኖታዊ ዝናቸውን ተጠቅመው በቅርባቸው ሰው እጮኛ ጭምር በወሲብ ሲወድቁ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም ። ቤተክርስቲያን ዛሬ የነውር ቤተመቅደስ ስትሆን መሪዎች ዝምታን መርጠዋል ። ዛሬ ነውር የቅዳሴን ያህል ተለምዷል ። እነ ፓስተር ዳዊት ሞላልኝ ከምዕመናኑ በሰበሰቡት ብር ውድ ቤት በላዩ ሲሰሩበት ፣ ቅንጡ መኪና ሲነዱበት ፣ ይህም አለበቃ ብሎ ሲያንጓጥጡት ምዕመኑ እነሱን እንደ አምላክ መልዕክተኛ ቆጥሮ ዝም ሲል እነ ዳንኤል ዓይን አውጥተው “ሞቼ ተነሳሁ” አሉ ።
እነተከስተ ደግሞ የወሲብ ዜማቸውን ያሰሙን ጀመር ። በሀይማኖት ገና ብዙ ዋጋ እንቀበላለን ። የሀይማኖት አባቶች በዚህ ደረጃ የወረዱት ሰዎች ” የሰይጣን ስራ ነው ” ብለው ከለላ ይሰጧቸዋል ። አስቦና አቅዶ በመጠጥ አደንዝዞ ልቅ ወሲብ የፈፀመን ሰው በሰይጣን ማሳበብ አስቂኝ ነው ። የሀይማኖት መሪዎች ፣ ሰባኪዎችን ፣ ዘማሪያንን በሰው ደረጃ አውርዶ ማሰብ ካልተቻለ መታለሉም ይቀጥላል ። ሁል ጊዜ የማይሰለጥነው አስተሳሰብ እንዲህ ያለውን ጋጠወጥነት ማውገዝ ሀይማኖቱን ማስወቀስ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው ። እነ ዘማሪያንና ፓስተር ግን ለምዕመናኑ ቀርቶ ለአምላክም አይመለሱም ።
No comments:
Post a Comment