Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 10, 2015

በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች የስደተኞችን ሻንጣ ዘረፉ

በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች የስደተኞችን ሻንጣ ዘረፉ


ከአንድ አመት በፊት የሳውዲ አረቢያ መንግስት በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች ግዛቱን ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠው የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ አይሌ ኢትዮጵያውያን ጅዳ እና ሪያድ ከተማ ወደ ሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ መጉረፋቸው ይታወሳል ። በወቅቱ ከነበረው ስረዓት አልበኝነት ህይወታቸውን ለመታደግ አቅሙ የቻለ ጎረምሳ ልብሶቹን በሻንጣ አጭቆ እግር አውጭኝ ሲል አይን ያልገለጹ ህጻናት ልጆቻቸውን በወጉ መሰብሰብ ያልቻሉ እናቶች ለክፉ ቀን ትሆነኛለች ብለው የሸመቷትን ወርቅ እና የተለያዩ ጌጣጌጦቻቸውን የያዘች አነስተኛ ሻንጣ አንጠልጥለው ከቀማኞች የታደገናል ወዳሉት በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በማቅናት ለተውሰኑ ቀናቶች ተጠልለው ሻንጣዎቻቸው በካርጎ ጭነት እንደሚላክ ቃል ተገብቶላቸው ለልጆቻቸው ተለዋጭ የረባ ጨርቅ እንኳን ሳይዙ ባዶ እጃቸውን ወደ ሃገር ቤት ማቅናታቸው ይነገራል ።
Jida
Jida 1
በወቅቱ በዚህ መልክ ወደ ቆንስላ ጽ/ቤት ቅጠር ግቢ የሚመጣውን ወገን ሃብትና ንበት በሃላፊነት ተረክቦ ወደ ሃገር መላክ የሚችል አካል ባለመኖሩ በጅዳ እና አካባቢው የሚኖሩ ታዋቂ ግለሰቦች ከዲፕሎማቱ ጋር በመተባበር አንድ ወገን ለወገን የሚል ኮሚቴ በማዋቀር ኢትዮጵያኑንን ወደ አህገር በሰላም እንዲገቡ ስፊ የማስተባበር ዘምቻ ይካሄድ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ ። ይህ ኮሚቴ ወደ ሀገር ተመላሽ ወገኖችን ስምና አድራሻ እየመዝገበ በአደራ ተቀብሎ ከሚሰበስበው ንብረት ባሻገር በተለያዩ ግዜያት በአሰሪዎቻቸው ተደብድበው ተድፍረውና ደሞዛቸው ተነጥቆ ወደ ቆንስላው ቅጠር ግቢ የሚመጡ እህቶች ጉዳያ ተድበስብሶና በደልን ተሸክመው ወደ ሃገር መሸኝት እንደሌለባቸው በማመን የቆንስላው ባለስልጣናት በዚህ ዙሪያ አንድ አይነት ሚና መጫወት እንደሚገባቸው እያደረገ በነበረው ግፌት ኮሚቴው ከተሰጠው ሃላፊነትና ተግባር አፈንግጦል በሚል ቅሬታ በአካባቢው የ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎችና የአሰሪ እና ሰራተኛ ኤጀንሲ ደላሎች በተፈጠረው አለመግባባት የማህበሩ መስራቾች በቆንስላው ዲፕሎማቶች ተእዛዝ ወደ ቆንስላው ግቢ እንዳይገቡ በመታገዳቸው የወገን ለወገን ህልውና ገና ከጅምሩ በአደራ የተረከበውን ንበረት ሜዳ ላይ በትኖ ይከስማል ።
መንገደኛ እና ሻንጣ በተለያዩበት የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የጎዞ መስተንግዶ አሳዛኝ ትራጀዲ በተፈጠረው ስረአት አልበኝነት የተጠቀሱትን ሻንጣዎች ከአደጋ ለመከላከል ባሉበት ሁኔታ ሸራ ለብሰው ቀሩ ። እህቶች ለአመታት ይደርስባቸው የነበረውን እንደወላፈን የሚፋጅ የአረብ ወይዛዝርት ቁጣ እና ግልምጫ ተቋቁመው ባገኙት ደሞዝ የሸመቱት ወርቅና የተለያየ ጌጣጌጦችን የያዙ ሻንጣዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት አቆመ በሚል ሰንካላ ምክንያት ወደ ሃገር እንዳይልኩ በቆንስላው ዲፕሎማቶች እገዳ ተጣለባቸው ። የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ቅጠር ግቢ ተቆልለው የሚታዩት እነዚህ ሻንጣዎች ለወራት ዝናብ እና ፀሃይ እይተፈራረቀባቸው ባለቤት አልባ ሆነው ደፍን አመት ካስቆጠሩ በኃላ ሰሞኑን በሻንጣዎቹ ላይ አስነዋሪና አስዛኝ ተግባር ተፈፀመ ። በተለይ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ግቢ ውስጥ ከተደረደሩ ሻንጣዎች ውስጥ የአባዛኛው ቁልፍ መስበሩን የሚናገሩ ውስጥ አውቂዎች ሻንጣዎቹ ላይ የተፈፀመው ዘረፋ የዲፕሎማቱ እጅ እንዳልበት በመረጃ ስደገፈው ይናገራሉ። የቆንስላ ግቢውን ጭር ማለት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ማታ ማታ በስብሰባ ሽፋን ያለወትሮቻው ቆንስላው ግቢ እያደሩ የሚወጡትን ከዲፕሎማቱ ጋር የቀርብ ግንኙነት ያላቸውን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አባላት ይጠረጥራሉ ።
​ይህ በዚህ እንዳለ ሰሞኑን የ ሰማያዊ «ማንዋል» ፓስፖርት የአገልግሎት ዘመን ማብቃቱን ተከትሎ ፓስፖርት ለማስለወጥና ለማሳደስ የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በተከስተው የባለጉዳዩች መጨናነቅ ዲፕሎማቱ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ቆንስላ ጽ/ቤት ለሚገባው ተስተናጋጅ የ3 ወር እና ከዚያ በላይ ቀጠሮ እይተሰጠው ሲሸኝ በሌላ አቅጣጫ ለሚስተናገድ ባለጉዳይ ከ 5 ቀን ባልበለጠ ግዜ ውስጥ ሁሉም ነገር እንዲምያልቅለት የሚናገሩ ባለጉዳዩች ዲፕሎማቱ እይሰጡ ባለው በሙስና የነቀዘ አገልግሎት ክፉኛ መማረራቸውን ይናገራሉ ፡፤ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልጋዩች በሚል ሽፋን ከዲፕሎማቱ ጋር ጥብቅ ቁረኝነት ያላቸው የዚህ ወንጀል ተባባሪ ደላሎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። በዚህ ዙሪያ ለማነጋገር በቀርቡ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ሃላፊ ሆነው የተሾሙትን አንባሳደር ውበሸትንም ሆነ ዲፕሎማት ሼሪፍ ኬሬን በአካል ለማገኘት ያደረኩት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials