Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, February 12, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ አባላቱን ስለ እስር ቤት አያያዝና መፍትሔዎች ስልጠና ሰጠ

ሰማያዊ ፓርቲ አባላቱን ስለ እስር ቤት አያያዝና መፍትሔዎች ስልጠና ሰጠ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ የፓርቲው አባላት በሚያከናውኗቸው እንቅስቃሴዎች በገዥው ፓርቲ በሚደረግባቸው እስር ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያስችል የእስረኛ አያያዝና መፍትሄዎች ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናው ‹‹አባላት ፓርቲው በሚሰጣቸው ኃላፊነት እና በሚያከናዉናቸው ተግባርት እንዲሁም የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ብቻ በመሆናቸው፣ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ተደጋጋሚ እስርት እና እንግልት ስለሚፈፀምባቸው ይህን በገዥው መንግስት በተደጋጋሚ የሚደርሰውን በደል በህግ ለመከላከል እንዲችሉ›› ለማድረግ ያሰበ መሆኑን የፓርቲው የህግ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ገልጸዋል፡፡
መሠረታዊ የሆኑ በህግ የተደነገጉ መብቶችን አስመልክቶ በተከታታይ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ የገለጹት ኃላፊው መብቶች በመንግስት ስለሚጣሱ አባላቱ መብታቸውን እንዲያውቁና መንግስት አባላትን በገፍ በሚያስርበት ወቅት ጠበቃ ለማቆም አስቸጋሪ በመሆመኑ በፍርድ ሂደቱም ለራሳቸው መብት እንዲከራከሩ ለማብቃት ነው ብለዋል፡፡
በስልጠናው ብሄራዊና ዓለም አቀፍ ህጎችም የተዳሰሱ ሲሆን አፋኝ አዋጆች፣ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረጉ ህገ ወጥ እስሮችና የእስር ቤት አያያዝ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም ከእነዚህ ተምረው የሚያጋጥማቸውን ችግሮች እንዴት መወጣት እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚያስጨብጥ እንደነበር አቶ ይድነቃቸው ገልጸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials