Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, February 26, 2015

«አፋን ኦሮሞ ስለማትናገሩ በኦሮሚያ መወዳደር አትችሉም» – ምርጫ ቦርድ


Tesfayeአቶ ምርቱ ጉታ ዋቅጅራ የአንድነት ፓርቲ የምስራቅ ቀጠና አደራጅ ነበሩ። የአዳማ ናዝሬት አንድነት ሊቀመንበርም ሆነው ሰርቷል። አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላ የአዳማ አንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ነበሩ።
ገዢው ፓርቲ ሕወሃት ፣ የአንድነትን ፓርቲ ሕጋዊነት ላደራጀው የተለጣፊው የትግስቱ ቡድን ሲሰጥ ፣ አቶ ምርቱ፣ አቶ ተስፋዬና በርካታ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ማሊያ ለብሰው ትግሉን ቀጠሉ፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ ሥር ለመወዳደር፣ አቶ ምርቱና እና አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላ በአዳማ አንድ ምርጫ ጣቢያ ለመመዝገብ ይሄዳሉ። ከብሔራዊ ቋንቋው ውጪ የክልሉን ቋንቋ ካልተናገራችሁ መመዝገብና ለምርጫ መወዳደር አትችሉም በመባላቸው ፣ በአገራቸው ለምርጫ የመመዝገብ መብታቸው ተነፈገ።
አዳማ ናዝሬት ኢትዮጵያዉያን ዘር፣ ቋንቋ፣ ኃይማናቶ ሳይለያያቸው በሰለም ፣ ተሰምማተው የሚኖሩባት ከተማ ናት። አዳማ/ናዝሬት የፍቅር ከተማ ናት። በዚያ የተወለዱ ወገኖች ራሳቸውን የሚያስተዋዉቁት ትግሬ፣ ጉራጌ፣ ኦሮሞ ብለው አይደለም። ናዝሬቶች ነን ብለው ነው። በዚያ ያለው ህዝብ አፋን ኦሮሞ ይናገራል፤ አማርኛ ይናገራል። ቋንቋ ከመግባቢያ መሳሪያነቱ ዉጭ አዳማዎች አይተቀሙበትም። ሆኖ ህወሃት ቋንቋን በመጠቀም አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ተጎጂ እንዲሆን በማድረግ፣ ለአንዱ ሰጥቶ ለአንድኑ በመንፈቅ፣ መቃቃርና ልዩነቶች እንዲመጡ ለማድረግ ፣ በናዝሬት/አዳማ የዘር ግጭት እንዲፈጠር ለመቀስቀስ ደፋ ቀና እያለ ነው።
ሕወሃት መርዛማ ፖለቲካውን ይኸው ላለፉት 24 አመታት ሲረጭ ነው የቆየው። የኦሮሚያ ክልል ሕግ መንግስትም ፣ በፌዴራል ሕገ መንግስቱ የተቀመጠዉን የዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብት በመናድ፣ ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ እንደሆነች፣ የኦሮሚያ የክልሉ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ብቻ እንደሆነና በኦሮሚያ ለመመረጥ አፋን ማወቅ እንደሚያስፈልግ ይደነግጋል። በኦሮሚያ የሚኖሩ ከ20 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሌሎች ብሄረሰቦች ፣ ኦሮሞ ነን የሚሉ ግን አፋን ኦሮሞ በደንብ የማያወቁ ኦሮሞዎች፣ የመመረጥ መብታቸውን ሙሉ ለሙሉ በወረቀት ላይ ያለው የኦሮሚያ ሕግ መንግስት ይጨፈልቀዋል።
በዚህም መሰረት አፋና ኦሮሞ መናገር በደንብ አትችሉም በመባላቸው፣ እነ ምርቱ ጉቱን ተስፋዬ ዋቅቶሎ የመመረጥ መብታቸዉን አጥተዋል።
ይሄ ዘር እየሉ ዜጎችን የመከፋፈል ተግባራት፣ በጥናትና ከማእከል በመመሪያ የሚደረግ እንደሆነ ብዙ መረጃዎች ያስረዳሉ። ለምሳሌ በቅርቡ የኢሕአዴግ አመራር አባላት ባደረጉት ግምገማ፣ የደቡብ ክልል አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ፣ የአማርኛ ተናጋሪዎች (አማሮች የሚሏቸውን) ከክልሎ በግፍ እንዲወጡና እንዲባረሩ ባደረጉበት ጊዜ፣ መመሪያ ከአቶ መለስ ዜናዊ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።
በግምገማው ወቅት «አማራን ባስወጣህበት የደቡብ ክልል መስተዳደር ጊዜህ ለክልሉ ነዋሪዎች ነፍጠኛ ከኛ ይወገዳል ብለህ ተናግረሃል” በሚል ከብአዴን ተወላጆች አስተያየት ሲሰጥ» አቶ ሽፈራው ” ከጠ/ሚኒስትሩ የተሰጠኝን ተልእኮ ነው በአግባቡ የተወጣሁት፣ ሌላ አልጨመርኩም አላስወጣሁም” በማለት ነበር የመለሱት።
ገዢው ፓርቲ በ እቅድ የዘር ከፋፋይ ፖለቲካውን ብዙ ገንዝበ መድቦ ለማሳፋፋት ቢሞክርም፣ የአዳማ/ናዝሬት ህዝብ ለመርዛማው የዘር ፖለቲካ እጅ አልሰጠም። በአስተሳሰቡ መጥቆ ሄዷል። አሁንም ፍቅሩን እና አንድነቱን ጠብቆ፣ እስላም ክርስቲያን ፣ አማራ ፣ ኦሮሞ ሳይባባል፣ ተስማምቶ በሰላም እየኖረ ነው። የአገዛዙ የከፋፍለህ ግዛ የጥላቻ ፖለቲካ እየተሸነፈ ነው። ፍቅርና ኢትዮጵያዊነት እያሸነፈ ነው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials