Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, February 1, 2015

TPLF assigns Selome tadesse as if Independent election candidate

ወይዘሪት ሰሎሜ ታደሰ የግል ተወዳዳሪ ሆና ምርጫ ልትቀርብ መሆኗን ይፋ አደረገች።
የቀድሞ የኢ-ቲቪና ሬዲዮ ዳይሬክተር የነበረቸው ሰሎሜ ታደሰ የወይዘሮ አዜብ ለሴቶች መብት መጨነቅ አንሶ እሷም የሴቶች መብት ጉዳይን ለማስከበር የፓርላማ ወንበር መያዝ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘችው በግሏ ምርጫ ለመወዳደር መወሰኗንና 5000 ፊርማ አሰባስባ ለምርጫ ቦርድ በማሳወቋ ለምርጫ እንደምትሳተፍ አሳውቃለች። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት አለም አቀፍ ቃል አቀባይ የነበረች ሲሆን አቶ በረከት ስምዖን በአቶ መለስ ዜናዊ የማስታወቂያ ሚኒስተር ሆነው ሲሾሙ ኤርትራዊ አለቃ እንደማትፈልግ ተናግራ በራሷ ፍላጎት ከስራ መልቀቋ ይታወሳል።
የተማረችው በቀድሞ ሶቪየት ህብረት በሌኒን ዩኒቨርሲቲና በMount Holyoke College MA.USA ነበረ። ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ ወይዘሪት ሰሎሜ በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ የአምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊ ሆና ተሹማለች። ወይዘሪት ሰሎሜ በትግራይ ተወላጅነቷና በድሮ መልኳ ብቻ እዚህ ደረጃ መድረሷ ብዙዎችን ያስገርማል። ከማስታወቂያ ሚኒስተር የመንግስት ደሞዝተኛ ሆና ከመስራቷ ሌላ ስራ ስትሰራ ታይቶ ባይታወቅም ዛሬ ከሌተና ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ጋር የራያ ቢራ ፋብሪካ ዋና ባለ አክሲዎን ነች። ብቸኛ ተወዳዳሪ ብትሆንም ገለልተኛ ግን አይደለችም። ሰሎሜ ታደሰ የህዋሃት እጩ ተወዳዳሪ ነች።Image result for selome tadesse
Selome Tadesse, independent election candidate
The ex-General Manager of Ethiopian Television & Radio Enterprise, Selome Tadesse, is on her way to becoming the first woman independent candidate in the general election on 24 May. She collected over 5,000 support signatures, more than four times the minimum needed to register with the National Electoral Board of Ethiopia (NEBE), and will run in the Bole District constituency, an industrial sector which includes Addis Ababa International Airport. Well-known internationally as she was the spokesperson for the Ethiopian government during the war with Eritrea, she founded the Network of Ethiopian Women's Associations (NEWA) which brought her a certain degree of recognition in her country.
She studied journalism at Lenin University in the former Soviet Union, followed by a BA in international relations from Mount Holyoke College (Massachusetts, USA). Of Tigrayan extraction, shortly after the change of regime in 1991 she was made press advisor to the Ethiopian ambassador in Washington, Berhane Gebre Christos, who is the present Secretary of State for Foreign Affairs. She also owns a big stake in Raya Brewery SC.

No comments:

Post a Comment

wanted officials