Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, February 23, 2015

ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ዕጩዎች ‹‹አትወዳደሩም›› ተባሉ

‹‹12 ፓርቲዎችን በዕጣ አልፋችኋል ለማለት ለ80 ፓርቲ ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?›› ወይንሸት ሞላ
‹‹ከምርጫ ቦርድ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡ መዝግቡ የተባልነውን መዝግበናል›› የምርጫ አስፈጻሚዎች
በአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሰማያዊ ፓርቲን ወክላ ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት ቀርባ የነበረችው ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ሌሎችም አዲስ አበባ ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡ ዕጩዎች ‹‹ዕጣው ስላልደረሳችሁ አትወዳደሩም›› መባላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ከወይንሸት ሞላ በተጨማሪ ብሌን መስፍንና አማኑኤል አዱኛ የተባሉ የሰማያዊ ዕጩዎች ‹‹ዕጣው አልደረሳችሁም›› ተብለው ከዕጩነት ውጭ ሆነዋል፡፡
ወይንሸት ሞላ ‹‹ዕጣው አልደረሰሽም›› በተባለችበት የምርጫ ጣቢያ የክልል ፓርቲዎችን የወከሉ ዕጩዎች አልፈዋል የተባሉ ሲሆን ወይንሸት ‹‹የክልል ፓርቲዎች ድምጽ ያሰባሰቡት በየክልሉ እንጅ አዲስ አበባ አይደለም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ሐገራዊ ፓርቲ ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ መራጭ የሌላቸው ፓርቲው በዕጣ አለፉ ተብሎ ሐገራዊ ፓርቲ የሆነው ሰማያዊ ወድቋል መባሉ ያለንበትን ስርዓት በድንብ የሚያጋልጥ ነው፡፡›› ስትል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
በወረዳ 7 17 ፓርቲዎችን የወከሉ ዕጩዎች የቀረቡ ሲሆን 12 ያለፉ ሲሆን ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች አምስት ፓርቲዎች ‹‹ዕጣው አልደረሳችሁም›› ተብለዋል፡፡ በወቅቱ ወይንሸት ሞላ ለምርጫ አስፈጻሚዎች ‹‹12 ፓርቲዎችን በዕጣ አልፋችኋል ለማለት ለ80 ፓርቲ ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?›› የሚል ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን የምርጫ አስፈጻሚዎችም ‹‹ይህ ከምርጫ ቦርድ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡ መዝግቡ የተባልነውን ነው የመዘገብነው›› የሚል መልስ እንደተሰጣት ገልጻለች፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ ዕጩዎች የታገዱበት ሲሆን በዛሬው ዕለት ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትም ‹‹ዕጣው አልደረሰህም›› ተብለው በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸው ይታወቃል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials