Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 24, 2015

የገዢው ፓርቲ ቃለ አቀባይ የነበረዉ ሽመልስ ከማል አሜሪካ ገባ ። ሊከዳቸው ነው ተባለ


ገዢው ፓርቲ እየተፍረከረከ ነው – ሽመልስ ከማል ከማል ሊከዳቸው ነው ተባለ



የገዢው ፓርቲ ቃለ አቀባይ የነበረዉና ጸያፍ ንግግሮች በመናገር የሚታወቀው ሽመለስ ከማል በህወሃቶች እንደ ሸንኮራ አገዳ ተመጦ እንደተተፋ ምንጮ ይገልጻሉ። ሕወሃቶች ዉስጥ ዉስጡን አገሪቷን እያደሙና እያጎሳቆሉ ላይ ላዩን የነርሱን የሽብር ተግባር በማስተዋወቅና በማብራራት፣ የነርሱም ቃለ አቀባይ በመሆን ለብዙ አመታት ያገለገለው ሽመልስ ከማል፣ ምናልባትም ከሕወሃት አባላት ቀጥሎ በዋናነት የሚጠላ ባለስልጣን እንደነበረ ብዙዎች ይገምታሉ።


የሽመለስ ከማል ወያኔን ከድቶ መሰደዱን የሚገልጹ ዜናዎች እየተሰሙ ቢሆንም፣ ከሽመለስ ከማል በይፋ ገና የተገለጸ ነገር የለም። ሽመለስ ከማል ከመድረኩ ከጠፋ ብዙ ጊዜ የሆኔ ሲሆን፣ ጊዜዉን ጫት በመቃም ያጠፋ እንደነበረም በስፋት ተዘግቧል።

ሽመለስ ከማል የቅንጅት መሪዎች ታስረው በነበረ ጊዜ አቃቤ ሕግ ከሳሽ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ሕዝባችንን ለማሸበር ሕወሃት እየተጠቀመበት ያለዉን የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግን ካረቀቁት ሰዎች መካከል አንዱ ነበር።

የሽመለስ ከማል አገር ለቆ መሄድ፣ በሕወሃት እና በሌሎች የኢሕአዴግ አባላት ዘንድ ትልቅ መቃቃርና አለመግባባት እንደተፈጠረ በርግጠኝነት የሚያመላከት መሆኑን ዉስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። በተለይም ከፓርላማው 6% በመቶ፣ በኢሕአዴግ ብሄራዊ ምክር ቤትና ፖሊት ቢሮ 25% ብቻ መቀመጫ ያላቸው ሕወሃቶች፣ አሁን እያታየ ባለ መልኩ፣ ፍጹም አምባገነናዊ በሆነ ሁኔታ፣ ሌሎችን ሳያማክሩ ፣ እርስ በርሳቸው በትግሪኛ ብቻ እየተናጋገሩ የሚወስኑት ዉሳኔ፣ ብዙዎችን እያበሳጨ እንደሆነ ዉስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። በተለይም በአራት የአገሪቷ ማእዘናት አንጋፋ የሆነውን የአንድነት ፓርቲ ጥቂት የሕወሃት አመራሮች፣ ከፓርላማዉም ሆነ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ዉሳኔ ዉጭ፣ በራሳቸው ቀጭን ትእዛዝ እንዲታገድ ማድረጋቸው ኢሕዴጎች ዉስጥ ትልቅ ዉይይት እየፈጠረ ነው።

እነ ዶር ቴዎድሮስ ያሉ ግለሰቦች፣ እርስ በርስ ያለው አለመስማማት የከረረ በመሆኑ፣ «እንደምንም ብለን ምርጫዉ በስልጣናችን ላይ ችግር እንደማያመጣ ካረጋገጥም በኋላ፣ ከዚህ በፊት ከነበረው የበለጠ የፓርላማ መቀመጫዎች ለታማኝ ተቃዋሚዎች በመልቀቅ ነገሮችን ትንሽ ከፈት እናደርጋለን” በሚል ነገሮችን ለማረገብ የሞከሩ ቢሆን፣ ሁኔታው አሁንም ዉስት ዉስጡን እየበሰለ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

አርአያ ተስፋማሪያም የጦመረዉን እንደሚከተለዉ ያንብቡ

ሽመልስ ከማል አሜሪካ ገባ ። የኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድ ዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ የመጣው በግሉ እንደሆነ አስታውቀዋል።
በዲሲ ቆይታ ካደረገ በኋላ ኒውዮርክ ወደሚገኘው ወንድሙ ዘንድ ያቀናው ሽመልስ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ለመቅረት ሃሳብ እንዳለውና እንደሚፈልግ ምንጮቹ አጋልጠዋል።
ሽመልስ ከማል – አፋኙን የፕሬስ ህግ በማርቀቅ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ፣ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ከህትመት ውጭ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች ላይ የሞት ቅጣት እንዲበየን በመጠየቅ፣ እነእስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት እንዲፈረድባቸው በማድረግ፣ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች እስር ቤት እንዲገቡና በሽብርተኝነት እንዲከሰሱ በማድረግ እንዲሁም ሙስሊሙንና ተቃዋሚዎችን በጅምላ በመስደብና በማንጓጠጥ፣ ብርቱካን ሚዴቅሳ ለ2 አመት በጨለማ እስር ቤት እንድትማቅቅ በመፍረድ..ወዘተ የመብት ረገጣ ያካሄደና በበርካታ ወገኖች ህይወት ላይ የጭካኔ ፍርድ ያሳለፈ እንደሆነ ይታወቃል።

Source
Zehabesha

No comments:

Post a Comment

wanted officials