Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, February 15, 2015

ኦብኮ በገዥው ፓርቲ ወከባ እየደረሰብኝ ነው አለ



‹‹በጋራ ምክር ቤቱ እየተጠቀምን አይደለም›› አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ የኦብኮ ሊቀመንበር



ኦብኮ ኢህአዴግን ጨምሮ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች የመሰረቱት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም የምክር ቤቱን ስምምነት በጣሰ መልኩ በአባላቱ ላይ ከፍተኛ ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ እና የጋራ ምክር ቤቱም ህጎቹን ለማስከበር አቅም ማጣቱን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጸዋል፡፡ የኦህዴድ ካድሬዎች የኦብኮን አባላት በማስፈራራት፣ ቤተሰቦቻቸውን በማሸማቀቅና በማዋከብ ከምርጫ እጩነታቸው ራሳቸውን እንዲያገሉ፣ ራሳቸውን ከምርጫው አናገልም ያሉትን በማሰርና ከስራ በማባረር እንዲሁም ንብረታቸውን በመዝረፍ ላይ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ቶሎሳ በፓርቲው አባላት ላይ የሚደርሰውን ወከባ ለምርጫ ቦርድና ለጋራ ምክር ቤቱ ቢያቀርቡም ሁለቱ አካላት መፍታት እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡


‹‹በኦህዴድ ካድሬዎች ወከባ የደረሰበት አባላትን ለምርጫ ቦርድ ሪፖርት በማድረጉ፣ ለምን በምርጫ ቦርድ ሪፖርት አደረክ በሚል የኦህዴድ ካድሬዎች ሌሊት ሰብረው ገብተው የሞባይል ሱቁን ዘርፈውታል፡፡›› ያሉት ሊቀመንበሩ ጫናው ከአቅማችን በላይ ሆኗል ብለዋል፡፡

አቶ ቶሎሳ አክለውም ‹‹ወደ ጋራ ምክር ቤቱ ስንገባ አባላቶቻችን ላይ የሚደርሰው ወከባና አፈና ይቀንሳል የሚል እምነት ነበረን፡፡ ሆኖም የጋራ ምክር ቤቱ ህጎቹን ለማስከበር አቅም የለውም፡፡ የጋራ ምክር ቤቱ የተለያዩ ምክንያት እየተጠቀሰ ወርሃዊ ስብሰባውን ማድረግ አልቻለም፡፡ ለይስሙላህ ካልሆነ በስተቀር ጠንክሮ ውጤት ያስመዘግባል የሚል ግምት የለኝም፡፡ ምንም እንኳ እንዲጠናከር ግፊት ብናደርግም እንደተባለው እየተጠቀምንበት አይደለም›› ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials