Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, February 9, 2015

ወያኔ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመጎብኘት ለጠየቁ የእንግሊዝ ፓርላማ አባላትን ፈቃድ ከለከለ


አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመስፈታት ወደ ኢትዮጵያ ሊያመራ የነበረው የእንግሊዝ ፓርላማ አባላት ቡድን “ወደ ኢትዮጵያ ሄደን አቶ አንዳርጋቸውን ለመጎብኘት እቅድ ነበረን፣ ነገር ግን ብንሄድም አቶ አንዳርጋቸውን መጎብኘት እንደማንችል ስለተነገረን ጉዟችንን ሰርዘናል”


በጀርሚ ኮርቢን የሚመራው የእንግሊዝ የፓርላማ ቡድን ልኡካን ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ አቶ አንዳርጋቸው
የሚለቀቅበትን ጉዳይ ለመነጋገር እቅድ አድርገው የነበረ ቢሆንም በእንግሊዝ የወያኔ ኤምባሲ አምባሳደር
ብርሃኑ ከበደ ከሎንዶን ከልኡኩ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ጉዞው እንደተሰረዘ ታውቋል::
ወደ አዲስ አበባ ሄደን አንዲን ለመጎብኘት በሚቀጥለው ሳምንት ያሰብነው ጉዞ በባለስልጣናት እውቅናና ፍቃድ
ባለማግኘቱ ልንሰርዘው ተገደናል ሲሉ የልኡኩ መሪ ተናግረዋል::ሎርድ ዶላኪያ በእንግሊዝ ፓርላማ
የፓርቲዎች ሕብረት የኢትዮጵያ ጉዳይ ምክትል ሊቀመንበር ከሚስተር ኮርቢን ጋር ሊያደርጉት ያሰቡት ጉዞን
አስመልክቶ አለመፈቀዱን ተቃውመውት ግልጽ የሆነ ሂደት እንዲኖር የጠየቁ ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ጠበቃ
ክሊቭ ስታፎርድ ስሚዝ አንዳርጋቸውን እንዲጎበኙ እንዲፈቀድ አጥብቀው የጠየኡ ሲሆን በዚህ ሳምንት ጉዳዩን
በፓርላማ እንደሚያነሱት ገልጸዋል::
የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወይዘሮ የምስራች ሃይለማርያም በእንግሊዝ የሚገኘውን የወያኔ ኤምባሲ እና
አምባሳደር በሰብአዊ መብት ገፈፋ የሚያደርጉ አለቆቻቸው የገደል ማሚቱ ሆነው ያገለግላሉ ሲሉ
ተችተዋል::በለንደን ዳውን ስትሬት የሚከበረው የአቶ አንዳርጋቸው የ60ኛ አመት የልደት በአል ለማክበር እና
አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የተሰበሰበውን ፊርማ ለጠቅላይ ሚኒስትር ካሜሮን ይሰጠሉ::ከዚሁ ጋር በተያያዘ
የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቶብሊስ ኢልውድ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ ንዝህላል መሆናቸውና
በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ አለማንሳታቸው ቃላቸውን በማጠፋቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ሲሆን
ባለፈው ወር በእንግሊዝ ውጪ ጉዳይ ዲፕሎማቶች መካከል ከፍተኛ አተካሮ ፈጥሮ እንደነበር
ይታወሳል::የእንግሊዝ ውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ እንዳሉት የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች የፓርላማ አባላቱን
የጠበቃውን እና የአማካሪውን ጉብኝት መከልከላቸው አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል:: —

Ethiopia has refused to allow a delegation of parliamentarians to visit a British dissident facing the death penalty in the African country.
A delegation led by Jeremy Corbyn, Mr Tsege’s constituency MP, was to visit Ethiopia in a bid to secure his release. But the trip was abandoned after a meeting with Ethiopian ambassador Berhanu Kebede in London last week.
Mr Corbyn told The Independent: “We had made plans to go and see him next weekend and they said we would be refused admission to the detention facility.”
Lord Dholakia, the vice-chairman of the all-party parliamentary group on Ethiopia, who was due to travel out with Mr Corbyn, said it was made clear that they would not be welcome. Mr Corbyn is demanding that the Ethiopian government allows Mr Tsege’s lawyer, Clive Stafford-Smith, the director of Reprieve, to visit him and will raise the issue in the Commons this week. The Ethiopian embassy in London has accused Mr Tsege – who came to Britain as a political refugee in 1979 – of being a member of a “terrorist organisation” which wants to “overthrow the legitimate government of Ethiopia”.
A spokesman for the Ethiopian embassy said: “The ambassador advised the parliamentarians that there was no need for them to go to Ethiopia as the case is being properly handled by the courts.”
Last night, Yemi Hailemariam, Mr Tsege’s partner and mother of their three children, accused the ambassador of being “a mouthpiece for his bosses who have no regard for basic human rights”. Mr Tsege’s family will go to Downing Street today – which is his 60th birthday – to hand in a petition calling on David Cameron to demand his return. It can also be revealed that the Foreign Office minister Tobias Ellwood broke a promise to Mr Tsege’s family that his case would be raised during the African Union summit in Ethiopia last month.
Mr Ellwood had pledged that senior officials would raise the case. But in an email sent to Ms Hailemariam last week, a government official admitted: “Access to Ethiopian ministers is extremely limited during the summit and so it wasn’t possible to have a bilateral meeting with senior officials who might have influence over the case.”
A spokesman for the Foreign Office said: “We remain deeply concerned about Ethiopia’s refusal to allow regular consular visits to Mr Tsege and his lack of access to a lawyer, and are concerned that others seeking to visit him have also been refused access.”
Source: The Independent

No comments:

Post a Comment

wanted officials