Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, February 19, 2015

“ዘመቻው በከፊል ተሳክቷል፤ ከጋዜጠኛ ተመስገን ጋር ተገናኝተናል”

“ዘመቻው በከፊል ተሳክቷል፤ ከጋዜጠኛ ተመስገን ጋር ተገናኝተናል”




(ኢ.ኤም.ኤፍ) ጋዜጠኛ ተመስገን የኢህአዴግን አሰራር በመቃወም ሃሳቡን ስለገለጸ “አሸባሪ” ተብሎ አሁን በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ነገሮችን የበለጠ ያከፋው ደግሞ ከቅርብ ግዜ ወዲህ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቤተሰቡም ሆነ በጓደኞቹ እንዳይጎበኝ መደረጉ ነበር። ከአንድ ወር በፊት ስንቅ ሊያቀብል የሄደው ወንድሙን ደብድበው፤ ምግቡን መሬት ላይ ደፍተው ገንዘቡን ጭምር ወስደው ከቃሊቲ እስር ቤት ያባረሩት መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም።
ጋዜጠኛውን በፈጠራ ወንጀል ማሰር ሳያንስ እንዲህ ያለ ግፍ መፈጸም ኢሰብአዊነት መሆኑን በመግለጽ በርካታ ውትወታዎች ተደርገው ነበር። በቅርቡም የህገ መንግስቱ አንቀጽ 21 እንዲከበር እና የእስረኛ ሰብአዊ መብት እንዲከበር የሚጠይቅ የበይነ መረብ ዘመቻ ተካሂዷል። ይህ ዘመቻ በከፊልም ቢሆን ውጤት ያሳየ ይመስላል። ለመጀመሪያ ግዜ የተመስገን ወንድም እስር ቤት ሄዶ እንዲጎበኝ ተፈቅዶለታል። ሆኖም ጋዜጠኛ ተመስገን አሁንም በከፍተኛ የህመም ዝቃይ ውስጥ ነው። ህክምና እንዳያገኝ ተደርጓል። ይህም ሁኔታ የበይነ መረቡ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላካች ነው። ለማንኛውም የዘመቻው አስተባባሪዎች የሰጡትን አጭር መግለጫ ከዚህ ቀጥሎ አቅርበናል።

በቅድሚያ ያለፈውን ሳምንት አብራችሁን ለነበራችሁ የበይነ-መረብ ዘማቾችና ወዳጆች ምስጋና ይድረስ፡፡
በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የምግብ የህክምናና የጎብኚ እግድ የተጣለው ከአንድ ወር በፊት ነበር፡፡ በዚህ የተቆጡ ቤተሰብና ወዳጆች ይህን መንግስታዊ ወንጀል ለማስቆም ይበጃል ያሉትን ሙከራ አድርገዋል፡፡ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በበይነ-መረብና በተቋማት ቢሮዎች ላይ የተደረገው አስጨናቂ ህግን የማስከበር ውትወታ የመጀመሪያውን ውጤት አይቷል፡፡ ተመስገንንም በአካል ለማየት ተችሏል፡፡
የሰብአዊ መብት ኮሚሽን መርማሪዎችና በርከት ያሉ አጃቢ ወታደሮች ባሉበት፣ ከወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ጋር ዛሬ የተገናኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ጤንነቱ አደጋ ላይ እንዳለ መረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ ቀደም የነበረው የጀርባ ህመም አላስተኛ ወዳለው እብጠት መቀየሩንና የግራ ጆሮውም መስማት ወደማይችልበት ደረጃ መድረሱ ታውቋል፡፡ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ለዝዋይ ማረሚያ ቤት ያቀረበው ጥያቄም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ በቦታው ለነበረው ወንድሙ ገልጾለታል፡፡ አያይዞም ያለቀናት በቆየው ያላቋረጠ ዘመቻ ልባዊ ወዳጅነትን፣ ስስትንና ወንድማዊነትን ላሳያችሁ ወገኖች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ምስጋና አቅርቧል፡፡
መጎብኘት እንደተፈቀደላቸው ከኮሚሽኑ መርማሪዎች በስልክ ማረጋገጫ ያገኙት ወንድሙና አንድ ወዳጁ ቢሆንም ሁለቱም ለመግባት የሚያስፈልገውን ምዝገባ ካሟሉ በኋላ የተመስገን ወዳጅ ተከልክሎ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ እንዲገባ መደረጉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials