Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, July 19, 2015

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ አሊ ረዲ በጀርመን ከ3600 ዶላር በላይ ተዘረፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ አሊ ረዲ በጀርመን ከ3600 ዶላር በላይ ተዘረፈ

asletagne* ዘራፊው ፓስፖርቱን መልሷል!
ኢትዮኪክ እንደዘገበው በጀርመን – ፍራንክፈርት የአውሮፖ የኢትዮጵያኖች የስፖርት እና ባህል ፌስቲቫል ላይ ከኢትዮጵያ ለተወከለው “የአበበ ቢቂላ” ቡድን የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ አሊ ረዲ ትላንት የገንዘብ እና ፖስፖርቱን የያዘበት ቦርሳ ጠፍቷል።
ጀርመን ፍራንክፈርት ከገባ ጀምሮ ከሆቴል ውጭ ከአሊ ተለይቶ የማያውቀው መለስተኛ ቦርሳ ትላንት በድንገት የፌስቲቫሉ ዝግጅት በሚካሄድበት ስፍራ ላይ በውስጡ 3600 የአሜሪካን ዶላር ከ900 ኤውሮ እና ከፓስፖርቱ ጋር ጠፍቷል።
በፌስቲቫሉ ስፍራ አሊ ረዲን ዛሬ አግኝተነው ስለ ጉዳዮ ጠይቀነው ሲመልስ ቦርሳውን በምን እና የት ቦታ ላይ ከጀርባው አውርዶ ይህ አጋጣሚ እንዴት እንደተፈጠረ ማስታወስ አለማቻሉን ጠቁሞ ይሁንና ገንዘቡን የወሰደው ግለሰብ ፓስፖርቱ መሬት ላይ ወርውሮት መገኘቱን ለኢትዮ ኪክ ተኗግሯል።
የአሊ ረዲ የገንዘብ መጥፋት ተከትሎ ከኢትዯጵያ አብረውት የተጓዙት እና በውድድሩ ላይ ከአንደኛ ዲቪዚዮን ለዋንጫ ፍፃሜ ደርሰው ዋንጫውን ባይሳኩም በሁለተኝነት ወደ ዋናው ዲቪዚዮን ያለፉት የአበበ ቢቂላ ቡድን ተጨዋቾች ለአሊ ጥቂት ገንዘብ ማዋጣቸው ተሰምቷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials