ወያኔ እንደለመደዉ ከተቃዋሚዎች ጋር ለማገናኘት እየጣረ ነዉ
የደርባን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሳሙኤል በዘራፊዎች በተተኮሰ ጥይት ተመተው ህይወታቸው አለፈች ፡፡ አዎ ይህንን በተንተራሰ መልኩ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ የወያኔ ስራ አስፈጻሚ መስሪያ ቤ/ት የህወሃት ቀኝ እጅ የኢቶፕያ ኢንባሲ በደቡብ አፍሪካ ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የወያኔ ደጋፊዎችን ” የናንተም እጣ ፋንታ ይህዉ ነዉ ” ። በሚል ዲስኩር የቄሱን አሟሟት ከፖለቲካ አመለካከት ጋር ለማገናኘት እየጣረ መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኖአል። በተለይም ያለፈዉ እሁድ በ17/07/2015 ደጋፊዎችን መርጦ የጠራዉ ፕሪቶሪያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ በኦሮሞያ ክልል አዳማ ናዝሪት ላይ የንግድ ምእከል ግንባታን በመስራት ዙሪያ ገንዘብ የመሰብሰብ ሙከራ አድርጎ የነበረ ሲሆን በተቸማሪ ፡ በእኚሁ የሐይማኖት አባት አሟሟት ዙሪያ መክሯል።
በደቡብ አፍሪካ በቅርቡ ( Ethiopia wenet ET ) በሚል የፌስ ቡክ አካዉንት ላይ እራሱ የወያኔ መንግስት ተቃዋሚንና ደጋፊን ለማጋጨት ሆን ብሎ በደቡብ አፍሪካ ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የራሱ ደጋፊዎችን ፎቶ በማዉጣት (ቀንደኛ የወያኔ ደጋፊዎች በህዝብ ደም የሚቀልዱ ) ናቸዉና ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ነቅቶ ይጠብቅ የሚል መንፈስ ያለዉ ሽብር ፈጥሮ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የእኚሁን አባት በዘራፊዎች የመገደል መንፈስ ከሌሎች ጋር በማዛመድ ችግሩን ወደተባባሰ ደረጃ እንዲደርስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ አመለከተ።
የደርባን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሳሙኤል አስከሬናቸዉ ዛሬ ወደ ሐገር ቤት የሚላክ መሆኑን የደረሰን መረጃ የመላከተ ሲሆን ለእኙሁ የተከበሩ አባት ህብረተሰቡ የተሰማዉን ሐዘን እየገለጸ ይገኛል።
አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ የወያኔ ደጋፊ (እኛ በጣም ግራ ተጋብተናል ከእንግዲህ የመደገፍ መንፈሳችን እጅግ ተጎድቷል በፌስ ቡክ ላይ የሚለቀቀዉ ፎቶዋችንን ከኢንባሲዉ የወጣ ለመሆኑ ማረጋገጥ አይጠበቅብንም ያም ሆኖ ግን ዛሬ ከሐይማኖት አባት ሞት ጋር የፖለቲካ አመለካከትን ማንጸባረቅና ህዝብን ደም ለማቃባት መጣር በጣም የሚያሳዝን ነዉ በማለት ገልጸዋል )
No comments:
Post a Comment