Gudish Weyane
ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት ሲባል ብቻ ባነጣጠረ መልኩ የወያኔ ቀንደኛ ደጋፊዎችን በፌስ ቡክ የመገናኛ ድህረ ገጽ ላይ እያሰራጨ ይገኛል፤ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ተቃዋሚዎችን መቆጣጠር ያቃተዉ የወያኔ ቡድን ሰላዮች ወደ ደቡብ አፍሪካ ከተመሙ ከ2010 የአለም ዋንጫ ወዲህ ምንም ማድረግ ባለማቻላቸዉ ይህ እቅድ ከወደ ሃገር ቤ/ት ተጠንቶ መምጣቱን ከዉስጥ የወጣዉ መረጃ ሲያመላክት እቅዱ ደጋፊዎችን ከተቃዋሚዎች ጋር በማላተም ወደ ከፋ ደረጃ አድርሶ ተቃዋሚዎችን አንገት ማስደፋት የሚቻልበት ሁኔታን መፍጠር ሲሆን በዚህም አፈጻጸም ዉስጥ በመጀመሪያ ቴድሮስ አድሐኖምን ወደ እዚያዉ ልኮ ስብሰባ በመጥራት ተሰብሳቢዎችን ወይም ደጋፊዎችን ፎቶ ግራፍ በማንሳት በራሱ በቴዶርስ አድሐኖም ፌስ ቡክ ላይ በማሰራጨት ማላተሙ የተጀመረ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ የግል ፌስ ቡክ አካዉንት በመክፈት እያንዳንዳቸዉን ደጋፊዎች ፎቶ ግራፋቸዉን አዋህዶ ደም መጣጮች እየተባሉ እንዲለቀቁና ይህን ያደረጉት ተቃዋሚዎች ናቸዉ የሚል ዉዥንብር ፈጥሮ ደጋፊዎችን ወደተፈለገዉ አቅጣጫ መምራት መሆኑን ከዉስጣቸዉ የተዝረከረከዉ መረጃ አመለከተ
ይህንን መረጃ እያሰራጨ የሚገኘዉ ፌስ ቡክ አካዉንት ኢትዮፕያዊነት (Ethiopia wenet ) በሚል ስም የተቀረጸ ሲሆን የወያኔ ደካማ ተንኮል የፈጠረዉ የተቃዋሚነት መንፈስ ያዘለ ወያኔ በራሱ ፈጥሮት የራሱ ደጋፊዎችን አደጋ ላይ የጣለበት ሁኔታን የፈጠረ ከመሆኑ ባሻገር በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ '' እኛ ምንም የምናጣዉ ነገር የለም አዎ እኛ የምንታገለዉ ለአላማ ነዉ አላማችንም እስከ ሞት ድረስ ነዉ፤ ወያኔና ደጋፊዎቹ ግን አላማቸዉ ህዝብን መበደልና መዝረፍ ወይም ሐገር ቤት ለሰሩት መሰረተ ልማት ነዉ የሚኖሩት ማን እንደሚጎዳ እንተያያለን ሲሉ '' ከደጋፊዎቹ በኩል ደግሞ መሸማቀቅና መደናበሩ እንዲሁም የፍራቻ ዛቻዎች በርክተዋል
በደንቡብ አፍሪካ የጆን ፎስታ ፖሊስ ስቴሽን የወንጀል ምርመራና ክትትል ክፍል ተጠሪ የሆኑ አንድ ኮነሬል በዚህ ጉዳይ ምክንያትክስ ለመመስረት ወደ ጣቢያዉ የሚመላለሱ ኢትዮጵያዊያኖች በመበርጅከታቸዉ የተነሳ ጉዳዩ በተናጥል እንዲታይ ለበላይ አካል ሙሉ መረጃዉን ማሳለፋቸዉ ተረጋግጦዋል
ፎቶ ግራፍ ቴድሮስ አድሐኖም በፌ ቡኩ የለቀቀዉ የጆሐንስበርግ ደጋፊዎች
( ጉዲሽ ወያኔ )
No comments:
Post a Comment