Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 20, 2015

የፕ/ር ብርሃኑ አስመራ ከገቡ ጀምሮ፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ኢሳት ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ

የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ "ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል መሬት ላይ ወርዶ መምራት ይገባል" በሚል እምነት በከፍተኛ ውጣ ውረድ ከአሜሪካ ኤርትራ መግባታቸው እንደተሰማ በአርበኞች ግንቦት7 ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ፣ አስመራ በሚገኘው የድርጅቱ ጽህፈት ቤት አቀባበል ያደረጉላቸው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ተናግረዋል።በዋና ጽህፈት ቤቱ የሚሰሩ የፖለቲካ እና የውጭ ግንኙነት ክፍል አባላት ለፕሮፌሰሩ በጋራ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የገለጸው ሻለቃ አክሊሉ፣ ከአባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በሰራዊቱ ውስጥ የታየው መነቃቃት ለነጻነት የሚደረገው ትግል እንዲፋጠን፣ በተለይም ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የሚደረገውን ተቀራርቦ የመስራት ድርድር እንዲፋጠን እንደሚያደርገው ሳለቃ አክሊሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል። ፕ/ር ብርሃኑ አስመራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል። የፕ/ር ብርሃኑ አስመራ መድረስ ዜና ይፋ ከሆነ ጀምሮ፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ኢሳት ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። አርበኞች ግንቦት7ትን ለመቀላቀል የሚጠይቀው ህዝብ እየጨመረ መምጣቱንም ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ፕ/ር ብርሃኑ ግንቦት7ትን በሊቀመንበርነት ሲመሩ ቆይተው ፣ አርበኞች ግንቦት7 ውህደት ከፈጸሙ በሁዋላ የውህዱ ድርጅት ሊቀመንበር ሆነዋል። በውህደቱ ላይ ለመገኘት የነበራቸው ውጥን ከጉዞ ሰነድ ጋር በተያያዘ ባለመሳካቱ፣ ለመሪነት የተመረጡት በሌሉበት ነው። ይሁን እንጅ በውህደቱ ወቅት ለጉባኤተኛው በስልክ ባስተላለፉት መልክት፣ አንዳንድ ችግሮች ተፈተው በቅርቡ በረሃ ወርደው እንደሚቀላቀሉዋቸው ቃል ገብተው ነበር። በምርጫ 97 በተደረገው ምርጫ አሸንፈው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ብርሃኑ፣ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ከሁለት አመት ላለነሰ ጊዜ በእስር ቤት አሳልፈዋል። ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው በክኔል ዩኒቨርስቲ በመምህርነት ሲያገለግሉ ቆይተው ከወራት በፊት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማእረግ አግኝተዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials